እግዚአብሔርም ከሰውነቱ ሕማምን ያርቅ ዘንድ ይወዳል፤ ብርሃንንም ያሳየዋል፤ በጥበቡም ይለየዋል፤ ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል። የብዙዎችንም ኀጢአታቸውን እርሱ ይደመስሳል።
ዘሌዋውያን 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልብሱንና ገላውን ባያጥብ ግን ኀጢአቱን ይሸከማል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብሱን ባያጥብ፣ ሰውነቱንም ባይታጠብ ግን ኀጢአት ሠርቷልና ይጠየቅበታል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ፥ ገላውንም ባይታጠብ ኃጢአቱን ይሸከማል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገላውን ባይታጠብና ልብሱን ባያጥብ ግን በኃጢአቱ ቅጣቱን ያገኛል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልብሱንና ገላውን ባያጥብ ግን ኃጢአቱን ይሸከማል። |
እግዚአብሔርም ከሰውነቱ ሕማምን ያርቅ ዘንድ ይወዳል፤ ብርሃንንም ያሳየዋል፤ በጥበቡም ይለየዋል፤ ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል። የብዙዎችንም ኀጢአታቸውን እርሱ ይደመስሳል።
የበላውም ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ነገር አርክሶአልና ኀጢአቱን ይሸከማል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።
“ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኀፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኀፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኀፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኀጢአቱን ይሸከማል።
“አንድ ሰው ቢበድል፥ የሚያምለውንም ቃል ቢሰማ፥ ምስክርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይናገር በደሉን ይሸከማል፤
በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም፤ ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቍርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም የበላ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል።
ጴጥሮስም፥ “መቼም ቢሆን አንተ እግሬን አታጥበኝም” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ እኔ እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለህም” ብሎ መለሰለት።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።