ይሁዳ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሰዎች የሚያጕረመርሙና ሌሎችን ሰዎች የሚከስሱ ናቸው፤ ክፉ ምኞቶቻቸውን ይከተላሉ፤ በራሳቸው ይታበያሉ፤ ጥቅም ለማግኘት ሲሉም ሌሎችን ይክባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሰዎች ሁልጊዜ የሚያጒረመርሙና በምንም ነገር የማይደሰቱ ናቸው፤ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው በትዕቢት ቃል የተሞላ ነው፤ የራሳቸውን ጥቅም በመፈለግ ሰውን ይለማመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፥ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል። |
በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፤ የሚያጕረመርሙም መታዘዝን ይማራሉ፤ ዲዳ አንደበትም ሰላም መናገርን ይማራል።”
ስለዚህም አንተና ማኅበርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ተሰብስባችኋል፤ በእርሱም ላይ ታጕረመርሙ ዘንድ አሮን ማንነው?”
በነጋውም የእስራኤል ልጆች ሁሉ፥ “እናንተ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ገድላችኋል” ብለው በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ከቀራጮችና ከኃጥኣን ጋር ለምን ትበላላችሁ? ትጠጡማላችሁ?” ብለው በደቀ መዛሙርቱ ላይ አንጐራጐሩ።
ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር እንደ አንጐራጐሩ በልቡ ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “ይህ ያሰናክላችኋልን?
በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጕረመረማችሁ፦ ‘እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞሬዎናውያን እጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን።
ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።