Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ጴጥሮስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከሁሉ አስቀድሞ ይህን ዕወቁ፤ በመጨረሻው ዘመን የራሳቸውን ክፉ ምኞቶቻቸውን የሚከተሉ ዘባቾች እየዘበቱ ይመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከሁሉ በፊት ይህን አስተውሉ፤ በመጨረሻው ዘመን እንደራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንደሚመጡ እወቁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከሁሉ በፊት ይህን አስተውሉ፤ በመጨረሻዎቹ ቀኖች የሚያፌዙና ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ዘባቾች ይመጣሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ጴጥሮስ 3:3
17 Referencias Cruzadas  

እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን በኀጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ፤” ብለዋችኋልና።


እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።


ነገር ግን በስ​ውር የሚ​ሠ​ራ​ውን አሳ​ፋሪ ሥራ እን​ተ​ወው፤ በተ​ን​ኰ​ልም አን​መ​ላ​ለስ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል በው​ሸት አን​ቀ​ላ​ቅል፤ ለሰ​ውም ሁሉ አር​አያ ስለ መሆን እው​ነ​ትን ገል​ጠን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ራሳ​ች​ንን እና​ጽና።


ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤


ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።


እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማቸዋል፤ ለትሑታን ግን ክብርን ይሰጣል።


“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤


በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ ዕውቀት ግን በብልሆች ዘንድ በቀላሉ ይገኛል።


ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።


በን​ጉ​ሦ​ቻ​ችን ቀን አለ​ቆች ከወ​ይን ጠጅ ሙቀት የተ​ነሣ ታመሙ፤ እነ​ር​ሱም ከዋ​ዘ​ኞች ጋር እጆ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ።


ኃጥእ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውም ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ በክ​ፋት የበ​ደ​ሉም ሁሉ ይነ​ቀ​ላ​ሉና፤


ስለ​ዚህ የተ​ጨ​ነ​ቃ​ችሁ ሰዎ​ችና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን ሕዝብ የም​ት​ገዙ አለ​ቆች ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


“እናይ ዘንድ፥ ሥራ​ውን ያፋ​ጥን፤ እና​ው​ቃ​ትም ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ምክር፥ ትምጣ” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


የሚ​ክ​ደ​ኝን፥ ቃሌ​ንም የማ​ይ​ቀ​በ​ለ​ውን ግን የሚ​ፈ​ር​ድ​በት አለ፤ እኔ የተ​ና​ገ​ር​ሁት ቃል እርሱ በመ​ጨ​ረ​ሻ​ዪቱ ቀን ይፈ​ር​ድ​በ​ታል።


በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደ​ረ​ገው፥ ሁሉ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት በልጁ ነገ​ረን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios