Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 32:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከሰው የተ​ነሣ አላ​ፍ​ር​ምና፥ ከሟች ሰውም የተ​ነሣ አላ​ፈ​ገ​ፍ​ግ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ለማንም አላደላም፤ ሰውንም አላቈላምጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በማንም ሰው ፊት ግን አላደላም፥ ማንንም አላቈላምጥም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በዚህ ጉዳይ ለማንም አላደላም፤ ማንንም አላቆላምጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለሰው ፊት ግን አላደላም፥ ሰውንም አላቈላምጥም።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 32:21
18 Referencias Cruzadas  

ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


ይህን ነገር እና​ገር ዘንድ እን​ድ​መጣ ይህን ምክር ያደ​ረገ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መል​አከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ጥበ​በኛ ነህ፤”


በስ​ውር ለሰው ፊት ብታ​ደሉ ዘለፋ ይዘ​ል​ፋ​ች​ኋል።


ከእ​ርሱ ወደ ኋላ ትመ​ለ​ሳ​ላ​ች​ሁን? እስኪ ራሳ​ችሁ ፍረዱ።


ጥቂት እን​ድ​ተ​ነ​ፍስ እና​ገ​ራ​ለሁ። ከን​ፈ​ሬ​ንም ገልጬ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


ለሰው ፊት ማድ​ላ​ትን አላ​ው​ቅም፤ ከሰ​ውም የተ​ነሣ የማ​ፍ​ረው ካለ ትሎች ይብ​ሉኝ።


ልቤም ንጹሕ ነገ​ርን ያስ​ባል፥ የከ​ን​ፈ​ሮ​ችም ማስ​ተ​ዋል ንጹሕ ነገ​ርን ይመ​ረ​ም​ራል።


እርሱ ግን የክ​ቡ​ርን ሰው ፊት አያ​ፍ​ርም። ለታ​ላ​ቁም ክብር መስ​ጠ​ትን አያ​ው​ቅም፥ ከፊ​ታ​ቸ​ውም አይ​ሸ​ሽም።


እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ጮኸ​ዋ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ች​ህም ራሳ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተ​ዋ​ልና።


የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ የሚቀበልም እርሱን ይቀበለዋል።


“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።


ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።


ደቀ ዛሙርታቸውንም ከሄሮድስ ወገን ጋር ላኩበት፤ እነርሱም “መምህር ሆይ! እውነተኛ እንደ ሆንህ በእውነትም የእግዚአብሔርን መንገድ እንድታስተምር እናውቃለን፤ ለማንምም አታደላም፤ የሰውን ፊት አትመለከትምና፤


በፍ​ር​ድም ፊት አትዩ፤ ለት​ል​ቁም፥ ለት​ን​ሹም በእ​ው​ነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታ​ድሉ፤ ፍርድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከ​ብ​ዳ​ችሁ እር​ሱን ወደ እኔ አም​ጡት፤ እኔም እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤


ፍር​ድን አታ​ጣ​ምም፤ ፊት አይ​ተ​ህም አታ​ድላ፤ ጉቦን አት​ቀ​በል፥ ጉቦ የጥ​በ​በ​ኞ​ችን ዐይን ያሳ​ው​ራ​ልና፥ የእ​ው​ነ​ት​ንም ቃል ያጣ​ም​ማ​ልና ጉቦ አት​ቀ​በል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos