La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 17:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ኢያ​ሱን፥ “እኛ ብዙ ሕዝብ ስን​ሆን እስከ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ባረ​ከን ለምን አንድ ክፍል፥ አን​ድም ዕጣ ብቻ ርስት አድ​ር​ገህ ሰጠ​ኸን?” ብለው ወቀ​ሱት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የዮሴፍ ዘሮች ኢያሱን፣ “ቍጥራችን ብዙ ነው፤ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባርኮናል፤ ታዲያ እንዴት ርስታችን አንድ ዕጣና አንድ ድርሻ ብቻ ሆነ?” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዮሴፍ ልጆች ነገድ ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንኩ እስከ አሁንም ጌታ ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ድርሻ አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ?”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የዮሴፍ ነገድ ወደ ኢያሱ ቀርበው “እግዚአብሔር ባርኮን ለበዛነው ለእኛ እንዴት አንድ ዕጣ ብቻ ሰጠኸን?” ብለው ጠየቁት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን፦ እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንሁ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ክፍል አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ? አሉት።

Ver Capítulo



ኢያሱ 17:14
12 Referencias Cruzadas  

አባ​ቱም እንቢ አለ፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አው​ቃ​ለሁ ልጄ ሆይ፥ አው​ቃ​ለሁ፤ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ ታላ​ቅም ይሆ​ናል፤ ነገር ግን ታናሽ ወን​ድሙ ከእ​ርሱ ይበ​ል​ጣል፤ ዘሩም ብዙ ሕዝብ ይሆ​ናል።”


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ብሎ ባረ​ካ​ቸው፥ “በእ​ና​ንተ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ተብሎ ይባ​ረ​ካል፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ኤፍ​ሬ​ምና እንደ ምናሴ ይባ​ር​ክህ።” ኤፍ​ሬ​ም​ንም ከም​ናሴ ፊት አደ​ረ​ገው።


እኔም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን እጅ በሰ​ይ​ፌና በቀ​ስቴ የወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ምርኮ ለአ​ንተ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ የተ​ሻ​ለ​ውን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።


ከም​ና​ሴም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለኤ​ፍ​ሬም አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


ከይ​ሳ​ኮር ነገድ የዮ​ሴፍ ልጅ ኢጋል፤


ለብ​ዙ​ዎቹ ብዙ ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ጥቂት ርስ​ትን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ። ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን ርስ​ታ​ቸ​ውን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።


ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ልጆች ወገ​ኖች ባሎ​ቻ​ቸ​ውን አገቡ፥ ርስ​ታ​ቸ​ውም በአ​ባ​ታ​ቸው ነገድ ጸና።


የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ርስ​ታ​ቸ​ውን ወረሱ።


ኢያ​ሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆ​ና​ችሁ፥ ተራ​ራ​ማው የኤ​ፍ​ሬም ሀገ​ርም ከጠ​በ​ባ​ችሁ ወደ ዱር ወጥ​ታ​ችሁ መን​ጥ​ራ​ችሁ አቅ​ኑ​አት” አላ​ቸው።