ኢያሱ 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ኢያሱም፥ “ብዙ ሕዝብ ከሆናችሁ፥ ተራራማው የኤፍሬም ሀገርም ከጠበባችሁ ወደ ዱር ወጥታችሁ መንጥራችሁ አቅኑአት” አላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ኢያሱም መልሶ፣ “ቍጥራችሁ ይህን ያህል በዝቶ ኰረብታማው የኤፍሬም ምድር እስከዚህ የሚጠብባችሁ ከሆነ፣ ወደ ፌርዛውያንና ወደ ራፋይም ምድር ወጥታችሁ ደኑን ለራሳችሁ መንጥሩ” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ብዙ ሕዝብስ ከሆንህ ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦህ እንደሆነ ወደ ዱር ወጥተህ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለአንተ ስፍራ መንጥር።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ኢያሱም መልሶ “ብዙዎች ከሆናችሁና ኮረብታማይቱ የኤፍሬም ምድር ትንሽ ከሆነችባችሁ፥ ፈሪዛውያንና ረፋያውያን ወደሚኖሩበት ምድር ሄዳችሁ ጫካውን መንጥሩ” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ኢያሱም፦ ብዙ ሕዝብስ ከሆንህ ተራራማውም የኤፍሬም አገር ጠብቦህ እንደ ሆነ ወደ ዱር ወጥተህ በፌርዛውያንና በራፋይም ምድር ለአንተ ስፍራ መንጥር አላቸው። Ver Capítulo |