ተነሡና ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ቀን ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው፥ ከመከራም አድኖ ላሻገረኝ ለእግዚአብሔር መሠውያን እንሥራ።”
ዮናስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ፤ ይቅርታቸውን ትተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን በምስጋና መዝሙር፣ መሥዋዕት እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እሰጣለሁ፤ ‘ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደኅንነት ከእግዚአብሔር ነው፤ ስለዚህ ከምስጋና መዝሙር ጋር መሥዋዕትን ለአንተ አቀርባለሁ፤ የተሳልኩትንም እሰጣለሁ።” |
ተነሡና ወደ ቤቴል እንውጣ፤ በዚያም በመከራዬ ቀን ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው፥ ከመከራም አድኖ ላሻገረኝ ለእግዚአብሔር መሠውያን እንሥራ።”
እንዲህም ሆነ፤ ከአራት ዓመት በኋላ አቤሴሎም አባቱን፥ “ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት በኬብሮን አደርግ ዘንድ ልሂድ።
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘለዓለማዊ መድኀኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘለዓለም አታፍሩምና አቷረዱም።”
የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፦ እግዚአብሔር ቸር ነውና፥ ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት የሚያመጡ ሰዎች ድምፅ እንደ ገና ይሰማል። የዚያችን ምድር ምርኮኞች ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ወንድሞቻችን፥ ሰውነታችሁን ለእግዚአብሔር ሕያውና ቅዱስ፥ ደስ የሚያሰኝም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እማልዳችኋለሁ። ይህም በዕውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።
ስለ ተሳልኸው ስእለት ሁሉ የአመንዝራዪቱን ዋጋና የውሻውን ዋጋ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አታቅርብ፤ ሁለቱም በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያጸይፉ ናቸውና።
በውኑ እንግዲህ በስሙ እናምን ዘንድ የከንፈሮቻችን ፍሬ የሚሆን የምስጋና መሥዋዕትን በየጊዜው ለእግዚአብሔር ልናቀርብ አይገባንምን?