Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከአ​ራት ዓመት በኋላ አቤ​ሴ​ሎም አባ​ቱን፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ስእ​ለት በኬ​ብ​ሮን አደ​ርግ ዘንድ ልሂድ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከአራት ዓመት በኋላም አቤሴሎም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት ለማድረስ ወደ ኬብሮን እንድሄድ ፍቀድልኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከአራት ዓመት በኋላም አቤሴሎም ንጉሡን እንዲህ አለው፤ “በኬብሮን ለጌታ የተሳልሁትን ስእለት ለማድረስ እንድሄድ ፍቀድልኝ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከአራት ዓመት በኋላ አቤሴሎም ንጉሥ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ንጉሥ ሆይ! ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን ስእለት ለመፈጸም ወደ ኬብሮን እንድሄድ ፍቀድልኝ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እንዲህም ሆነ፥ ከአራት ዓመት በኋላ አቤሴሎም ንጉሡን፦ ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት ለመስጠት ወደ ኬብሮን፥ እባክህ፥ ልሂድ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 15:7
10 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ ለጠ​ብና ለክ​ር​ክር ትጾ​ማ​ላ​ችሁ፤ ድሃ​ው​ንም በጡጫ ትማ​ታ​ላ​ችሁ፤ በም​ት​ጮ​ኹ​በት ጊዜ ድም​ፃ​ችሁ እን​ዲ​ሰማ ለእኔ ትጾ​ማ​ላ​ች​ሁን? ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እን​ደ​ም​ት​ጾ​ሙት አት​ጾ​ሙም።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ “ሂዱ፤ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ” አላቸው።


የኃጥኣን መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ በክፋት ያቀርቡታልና።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም ኰብ​ልሎ ወደ ጌድ​ሶር ሄደ፤ በዚ​ያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀ​መጠ።


ሳሙ​ኤ​ልም የዘ​ይ​ቱን ቀንድ ወስዶ በወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ቀባው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳ​ዊት ላይ መጣ። ሳሙ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ወደ አር​ማ​ቴም ሄደ።


ለዳ​ዊ​ትም ወን​ዶች ልጆች በኬ​ብ​ሮን ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ በኵ​ሩም ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም የተ​ወ​ለ​ደው አም​ኖን ነበረ።


ሁለ​ተ​ኛ​ውም ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቤ​ግያ የተ​ወ​ለ​ደው ዶሎ​ሕያ ነበረ። ሦስ​ተ​ኛ​ውም ከጌ​ድ​ሶር ንጉሥ ከቶ​ል​ሜ​ልም ልጅ ከመ​ዓክ የተ​ወ​ለ​ደው አቤ​ሴ​ሎም ነበረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios