የገባላቸውንም ቃል ኪዳን ሁሉ አልጠበቁም። ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ከንቱም ሆኑ፤ እንደ እነርሱም እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።
ዮናስ 2:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ትግባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከንቱ በሆኑ ጣዖቶች ላይ የሚንጠለጠሉ፣ ሊያገኙ የሚገባቸውን ጸጋ ያጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ ጌታን አሰብሁት፤ ጸሎቴም ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሐሰት አማልክትን የተከተሉ ሁሉ፥ ለአንተ ያላቸውን ታማኝነት ትተዋል። |
የገባላቸውንም ቃል ኪዳን ሁሉ አልጠበቁም። ከንቱ ነገርንም ተከተሉ፤ ከንቱም ሆኑ፤ እንደ እነርሱም እንዳይሠሩ ያዘዛቸውን በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ።
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገሮችን አድርገዋልና፤ የሕይወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተውኛል፥ የተነደሉትን ውኃውንም ይይዙ ዘንድ የማይችሉትን ጕድጓዶች ለራሳቸው ቈፍረዋል።