Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮናስ 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራ​ሮች መሠ​ረት ወረደ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችዋ ወደ ተዘጉ ምድር ወረ​ድሁ፤ አቤቱ ፈጣ​ሪዬ! ሕይ​ወቴ ጥፋት ሳያ​ገ​ኛት ወዳ​ንተ ትውጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ነፍሴ በዛለች ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን ዐሰብሁ፤ ጸሎቴም ወደ አንተ፣ ወደ ቅዱስ መቅደስህ ዐረገች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ተራሮች መሠረት ወረድሁ፥ የምድር መወርወሪያዎችዋ ለዘለዓለም ተዘጉብኝ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ አንተ ግን ሕይወቴን ከጉድጓድ አወጣሃት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሕይወቴ እየተዳከመ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔርን አስታወስኩ፤ ወደ አንተ ወደ አምላኬ ጸለይኩ፤ ጸሎቴም ወደ ቤተ መቅደስህ ወደ አንተ መጣ።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 2:7
23 Referencias Cruzadas  

አወ​ጣጡ ከሰ​ማ​ያት ዳርቻ ነው፥ መግ​ቢ​ያ​ውም እስከ ዓለም ዳርቻ ነው፤ ከት​ኩ​ሳ​ቱም የሚ​ሰ​ወር የለም።


ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ተነ​ሥ​ተው ሕዝ​ቡን ባረኩ፤ ድም​ፃ​ቸ​ውም ተሰማ፥ ጸሎ​ታ​ቸ​ውም ወደ ቅዱስ ማደ​ሪ​ያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


አቤቱ፥ ሰማ​ዮ​ች​ህን ዝቅ ዝቅ አድ​ር​ጋ​ቸው፥ ውረ​ድም፤ ተራ​ሮ​ችን ዳስ​ሳ​ቸው፥ ይጢ​ሱም።


“ምላ​ሳ​ች​ንን እና​በ​ረ​ታ​ለን፤ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ችን የእኛ ናቸው፥ ጌታ​ችን ማን ነው?” የሚ​ሉ​ትን።


ስለ ወን​ዶ​ችና ስለ ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውም የሕ​ዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበ​ርና ሕዝቡ ሊወ​ግ​ሩት ስለ ተና​ገሩ ዳዊት እጅግ ተጨ​ነቀ፤ ዳዊት ግን በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራሱን አጽ​ናና።


ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም።


ምድር ሁላ ለአ​ንተ ትሰ​ግ​ዳ​ለች፥ ለአ​ን​ተም ትገ​ዛ​ለች፥ ለስ​ም​ህም ትዘ​ም​ራ​ለች።


በነ​ፍ​ሳ​ችሁ ዝላ​ችሁ እን​ዳ​ት​ደ​ክሙ፥ ከኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች በደ​ረ​ሰ​በት እን​ዲህ ባለ መቃ​ወም የጸ​ና​ውን እስኪ ዐስ​ቡት።


እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል።


እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ ስሙ፥ ምድርም ሙላዋም ታድምጥ፥ ጌታ እግዚአብሔርም፥ እርሱም በቅዱስ መቅደሱ የሆነ ጌታ፥ ይመስክርባችሁ።


ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣል​ኸኝ፥ ፈሳ​ሾ​ችም ከበ​ቡኝ፤ ማዕ​በ​ል​ህና ሞገ​ድህ ሁሉ በላዬ ዐለፉ።


ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤


በአ​ንተ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ንን ሁሉ እን​ወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለን፥ በስ​ም​ህም በላ​ያ​ችን የቆ​ሙ​ትን እና​ዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለን።


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።


ጠላት ነፍ​ሴን ከብ​ቦ​አ​ታ​ልና ሕይ​ወ​ቴ​ንም በም​ድር ውስጥ አዋ​ር​ዶ​አ​ታል፥ ቀድሞ እንደ ሞተ ሰው በጨ​ለማ አኖ​ሩኝ።


ሰው​ነ​ቴ​ንም እን​ዳ​ት​ጠፋ ይቅር አል​ሃት፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሁሉ ወደ ኋላዬ ጣልህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios