ኢዩኤል 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይኑ ደርቆአል፤ በለሱም ጠፍቶአል፤ ሮማኑና ተምሩ፥ እንኮዩም፥ የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይኑ ደርቋል፤ የበለስ ዛፉም ጠውልጓል፤ ሮማኑ፣ ተምሩና እንኮዩ፣ የዕርሻው ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ ስለዚህ ደስታ፣ ከሰው ልጆች ርቋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የወይን ተክሎችና የበለስ ዛፎች ጠውልገዋል፤ ሮማኑ፥ ተምሩና እንኰዩ፥ ሌሎችም የፍራፍሬ ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፤ በዚህም ምክንያት በእርግጥ ደስታ ከሰው ልጆች ርቆአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይኑ ደርቆአል፥ በለሱም ጠውልጎአል፥ ሮማኑና ተምሩ እንኰዩም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል፥ ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል። |
በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በወንድሞች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው።
ደስታና ሐሤትም ከወይን ቦታሽ ተወስዶአል፤ በወይንሽም ቦታዎች ፈጽመው ደስ አይላቸውም፤ በመጥመቂያውም ወይንን አይረግጡም፤ ረጋጮቹን አጥፍቻለሁና።
ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞአብ ምድር ጠፍተዋል፤ ወይን ከመጥመቂያው ጠፍቶአል፤ በነግህ የሚጠምቁት የለም፤ በሠርክም የሚያደርጉት የእልልታ ድምፅ የለም።
ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፣ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆም መጡ፤ አዩኣትም፤ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፤ በመሎጊያም ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።