Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐጌ 2:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ዘር በጎተራ ገና ይኖራልን? ወይንና በለስ ሮማንና ወይራ አላፈሩም፣ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በጐተራ የቀረ ዘር አሁንም ይገኛልን? የወይኑና የበለሱ ዛፍ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ እስካሁን አላፈሩም። “ ‘ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ።’ ”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ዘር በጎተራ አሁንም አለን? ወይንና የበለስ ዛፍ ሮማንና የወይራ ዛፍ አላፈሩም፤ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አሁን ለዘር የሚሆን እህል በጐተራ ባይኖር የወይንና የበለስ፥ የሮማንና የወይራም ተክል ሁሉ ገና ፍሬ ባይሰጥም ከዚህ ቀን ጀምሮ እኔ በረከትን እሰጣችኋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ዘር በጎተራ ገና ይኖራልን? ወይንና በለስ ሮማንና ወይራ አላፈሩም፥ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ሐጌ 2:19
19 Referencias Cruzadas  

ይስ​ሐ​ቅም በዚ​ያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው።


ዘር​ህ​ንስ ይመ​ል​ስ​ልህ ዘንድ፥ በአ​ው​ድ​ማ​ህስ ያከ​ማ​ች​ልህ ዘንድ ትታ​መ​ነ​ዋ​ለ​ህን?


ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የሠራ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ምሕ​ረ​ቱን ይሰ​ጣል፥ ምድ​ርም ፍሬ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች።


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


የካ​ህ​ና​ቱ​ንም የሌ​ዊን ልጆች ሰው​ነት ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ታ​ለሁ፤ አረ​ካ​ታ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤም ከበ​ረ​ከቴ ይጠ​ግ​ባል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወይኑ ደር​ቆ​አል፤ በለ​ሱም ጠፍ​ቶ​አል፤ ሮማ​ኑና ተምሩ፥ እን​ኮ​ዩም፥ የም​ድ​ርም ዛፎች ሁሉ ደር​ቀ​ዋል፤ ደስ​ታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆ​አል።


የሚ​መ​ለ​ስና የሚ​ጸ​ጸት እንደ ሆነ፥ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ህ​ልና የመ​ጠጥ ቍር​ባን የሚ​ሆን በረ​ከ​ትን በኋላ የሚ​ያ​ተ​ርፍ እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል?


እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


እጅ​ህን በም​ት​ጥ​ል​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ዚህ በሥ​ራህ ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃ​ልና ፈጽ​መህ ስጠው፤ የለ​መ​ነ​ህ​ንም ያህል አበ​ድ​ረው፤ በሰ​ጠ​ኸ​ውም ጊዜ በል​ብህ አት​ጸ​ጸት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ሳት፥ በን​ዳ​ድም፥ በጥ​ብ​ሳ​ትም፥ በት​ኵ​ሳ​ትም፥ በድ​ር​ቅም፥ በዋ​ግም፥ በአ​ረ​ማ​ሞም ይመ​ታ​ሃል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ያሳ​ድ​ዱ​ሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos