ኢዮብ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀን ጨለማ ያገኛቸዋል፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ ገና በእኩለ ቀን፥ በሌሊት ጨለማ ውስጥ እንዳሉ ሆነው ይደናበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። |
“እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? በምድር ላይ ሳሉ አላስተዋሉም፥ የቅንነት መንገድንም አላዩም። በአደባባይዋም አልሄዱም።
እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመሱ፤ ዐይንም እንደሌላቸው ተርመሰመሱ፤ በቀትርም ጊዜ በመንፈቀ ሌሊት እንዳለ ሰው ተሰናከሉ፤ እንደ ሙታንም ይጨነቃሉ።
ዕውር በጨለማ እንደሚዳብስ በቀትር ጊዜ ትዳብሳለህ፤ መንገድህም የቀና አይሆንም፤ በዘመንህም ሁሉ የተገፋህ፥ የተዘረፍህም ትሆናለህ፤ የሚረዳህም የለም።