ኢዮብ 23:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከትእዛዙም አላለፍሁም፤ ቃሉን በልቤ ሰውሬአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣ የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥ የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ትእዛዞች አልወጣሁም፤ ቃሉንም በልቤ ውስጥ ጠብቄአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከንፈሩ ትእዛዝ አልተመለስሁም፥ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ። |
ቃልህ ተገኝቶአል፤ እኔም በልችዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ሆይ! ቃልህን የከዱ ሰዎችን አጥፋቸው፤ ስምህ በእኔ ላይ ተጠርትዋልና፥ ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነኝ።
ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ምግባቸውን በየጊዜው ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው በቤተሰቡ ላይ የሚሾመው ደግ ታማኝና ብልህ መጋቢ ማን ይሆን?
የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠረጠረው ዕለት፥ ባላወቀውም ሰዓት መጥቶ ከሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርገዋል።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፥ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።
ጌታችን ኢየሱስም ያመኑበትን አይሁድ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተም በቃሌ ጸንታችሁ ብትኖሩ በእውነት ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ።
የደቀ መዛሙርትንም ልቡና አጽናኑ፤ በሃይማኖትም እንዲጸኑ፦“ በብዙ ድካምና መከራ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንገባ ዘንድ ይገባናል” እያሉ መከሩአቸው።
ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።