ኢዮብ 18:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጭኖቹ ይበሰብሳሉ። ሞትም መልካም ሕዋሶቹን ይበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደዌ ቈዳውን ይበላል፤ የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውነቱ ክፍሎች ይጠፋሉ፥ የሞትም የበኩር ልጅ ሰውነቱን ይበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሽታ ሰውነቱን ያመነምነዋል፤ ሞትም ጨርሶ ይረከበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውነቱ ብልቶች ይጠፋሉ፥ የሞትም በኵር ልጅ ብልቶቹን ይበላል። |
“ሮቤል እርሱ የበኵር ልጄና ኀይሌ፥ የልጆችም መጀመሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አንገቱንም አደነደነ። ጭንቅ ነገርንም አደረገ።
ድሆችም በውስጣችሁ ይሰማራሉ፤ ድሆች ሰዎችም በሰላም ያርፋሉ፤ ዘራችሁንም ረኃብ ያጠፋቸዋል፤ ከእናንተም የቀሩት ያልቃሉ።
እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
አየሁም፤ እነሆም ሐመር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።