ኤርምያስ 9:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጥነውም ሙሾ ያሙሹላችሁ፤ ዐይኖቻችሁም እንባን ያፍስሱ፤ ከዐይኖቻችሁም ሽፋሽፍቶች ውኃ ይፍለቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ፈጥነው ይምጡ፤ ዐይኖቻችን እንባ እስኪያጐርፉ፣ ሽፋሽፍቶቻችንም ውሃ እስኪያመነጩ፣ ስለ እኛ ሙሾ ያውርዱልን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዐይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ያነሳሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም እንዲህ አሉ፦ “ዐይናችን በእንባ እንዲርስ፥ በጉንጫችንም እንባው እንዲወርድ፥ አስለቃሾች በቶሎ ሙሾ እንዲያወጡ ንገሩአቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ ፈጥነው ለእኛ ልቅሶውን ይያዙ። |
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
“እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዐይኖቻችሁ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባን ያፍስሱ።
ነገር ግን ከትንሽነታችን ጀምሮ የአባቶቻችንን ሥራ፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም፥ እፍረት በልቶባቸዋል።
ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኀጢአት ሠርተናልና፥ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና በእፍረታችን ተኝተናል፤ ውርደታችንም ሸፍኖናል።”
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
“እግዚአብሔር የቍጣውን ትውልድ ጥሎአልና፥ ትቶታልምና ጠጕርሽን ቈርጠሽ፥ ጣዪው፤ በከንፈሮችሽም ሙሾ አውርጂ።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
እናንተ ሴቶች ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጆሮአችሁም የአፉን ቃል ትቀበል፤ ለሴቶች ልጆቻችሁም ልቅሶውን፥ እያንዳንድዋም ለባልንጀራዋ ዋይታን ታስተምር።
ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ እንባዋም በጉንጭዋ ላይ አለ፤ ከሚያፈቅሩአት ሁሉ የሚያጽናናት የለም፤ ወዳጆችዋም ሁሉ ወነጀሉአት፤ ጠላቶችም ሆኑአት።
ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?
ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፤ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፤ የዐይንሽንም ብሌን አታቋርጪ።
ስለዚህ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በየአደባባዩ ሁሉ ላይ ዋይታ ይሆናል፤ በየመንገዱም ሁሉ ላይ ወዮ ወዮ ይባላል፤ ገበሬዎቹም ወደ ልቅሶ፥ አልቃሾቹም ወደ ዋይታ ይጠራሉ።