በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፥ “እነሆ፥ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እናጠጣው፤ አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።”
ኤርምያስ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸውም ጊዜ ይዋረዳሉ፤ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ጸያፉ ተግባራቸው ዐፍረዋል እንዴ? የለም! በጭራሽ አላፈሩም፤ ዕፍረት ምን እንደ ሆነ እንኳ አያውቁም። ስለዚህ ከወደቁት ጋራ ይወድቃሉ፤ በሚቀጡ ጊዜ ይዋረዳሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ሆይ! ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር ስታደርጉ ጥቂት ኀፍረት ተሰምቶአችሁ ነበርን? ኀፍረት ሊሰማችሁ ቀርቶ ዐይናችሁ እንኳ ሰበር አላለም፤ ስለዚህ ሌሎች እንደ ወደቁ እናንተም ትወድቃላችሁ፤ እኔ በምቀጣችሁ ጊዜ ፍጻሜአችሁ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፥ “እነሆ፥ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እናጠጣው፤ አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።”
ሕዝቡ እንደ ካህኑ፥ ባሪያውም እንደ ጌታው ባሪያይቱም እንደ እመቤቷ፥ የሚሸጠውም እንደሚገዛው፥ ተበዳሪውም እንደ አበዳሪው፥ ዕዳ ከፋዩም እንደ ዕዳ አስከፋዩ ይሆናል።
ዛሬም ክብራቸው ተዋርዷልና፥ ፊታቸውም አፍሯልና ኀጢአታቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ኀጢአት ተቃወመቻቸው፤ በላያቸውም ተገልጣ ታወቀች።
ስለዚህ እግዚአብሔር በስሜ የሐሰት ትንቢት ስለሚናገሩ ነቢያት ስላላክኋቸው፦ በዚህች ሀገር ሰይፍና ረሃብ አይሆንም ስለሚሉ ነቢያት እንዲህ ይላል፥ “እነዚያ ነቢያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።
ስለዚህ መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ትሆንባቸዋለች፤ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
ርኩስ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ ውርደትንም አላወቁም፤ ስለዚህም ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳድራለሁ፤ አባቶችና ልጆችም በአንድነት ይታመማሉ፤ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ።
እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፣ ክፋትን አያደርግም፣ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፣ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ እግራቸው በሚሰናከልበት ጊዜ፥ የጥፋታቸው ቀን ቀርቦአልና፥ የተዘጋጀላችሁም ፈጥኖ ይደርስባችኋልና።
እነዚህም ፍጻሜያቸው ለጥፋት የሆነ፥ ሆዳቸውን የሚያመልኩ፥ ክብራቸውም ውርደት የሆነባቸው፥ ምድራዊዉንም የሚያስቡ ናቸው።