ኤርምያስ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 አዝመራቸውን ይሰበስባሉ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ የለም፤ ቅጠልም ይረግፋል፤ ሰጠኋቸው፤ አለፈባቸውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 “ ‘ያመረቱትን ሁሉ እወስድባቸዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ተክል ላይ የወይን ፍሬ አይኖርም፤ በበለስ ዛፍ ላይ የበለስ ፍሬ አይገኝም፤ ቅጠሎቻቸውም ይረግፋሉ። የሰጠኋቸው በሙሉ፣ ከእነርሱ ይወሰድባቸዋል።’ ” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፤ የሰጠኋቸሁም ይጠፋባቸዋል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 “ገበሬ ሰብሉን እንደሚሰበስብ ሕዝቤን ልሰበስብ ፈለግኹ፤ እነርሱ ግን ዘለላ እንደሌለው የወይን ተክል ፍሬ አልባ እንደ ሆነ የበለስ ዛፍና ቅጠሉ እንደ ረገፈ ተክል ሆኑብኝ፤ በዚህ ምክንያት የሰጠኋቸውን ምድር ባዕዳን እንዲወስዱባቸው አደረግሁ።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በወይን ላይ ፍሬ፥ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም፥ ቅጠልም ይረግፋል፥ የሚያልፉባቸውንም ሰጠኋቸው። Ver Capítulo |