ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም በእሳት ሥዉአቸው፤ ምዋርተኞችና አስማተኞችም ሆኑ፤ ያስቈጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ።
ኤርምያስ 7:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መሥዊያዎች ሠርተዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ያላዘዝኋቸውን፣ ከቶም ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት አቃጥለው ለመሠዋት በሄኖም ልጅ ሸለቆ የቶፌትን መስገጃ ኰረብቶች ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል፥ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያሉትን የቶፌት መስገጃዎችን ሠረተዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት እያቃጠሉ መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ በሂኖም ሸለቆ ውስጥ ‘ቶፌት’ ተብሎ የሚጠራ መሠዊያ ሠርተዋል፤ ይህም እኔ ያላዘዝኳቸውና በፍጹምም ያላሰብኩት ነገር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ያለችውን የቶፌትን መስገጃዎች ሠረተዋል። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም በእሳት ሥዉአቸው፤ ምዋርተኞችና አስማተኞችም ሆኑ፤ ያስቈጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ለማድረግ ራሳቸውን ሸጡ።
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
በዚያም የነበሩትን የኮረብታውን መስገጃዎች ካህናት ሁሉ በመሠዊያዎቹ ላይ ገደላቸው፥ የሰዎቹንም አጥንት በመሠዊያዎቹ ላይ አቃጠለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ተመለሰ።
ደግሞም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለምስሉ ሠዋ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት እንዳሳደዳቸው እንደ አሕዛብም ክፉ ልማድ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
እናንተ በለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣዖት ደስ የምትሰኙ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ልጆቻችሁን የምትሠዉ፥ እናንተ የጥፋት ልጆችና የዐመፀኞች ዘሮች አይደላችሁምን?
አንቺስ፦ አልረከስሁም፤ በዓሊምንም አልተከተልሁም፤ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፤ ያደረግሽውንም ዕወቂ። ማታ ማታ በመንገዶች ትጮኻለች፤
ይሁዳን ወደ ኀጢአት እንዲያገቡት፥ ይህን ርኵሰት ያደርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን መሠዊያዎች ለበዓል ሠሩ።”
እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ እንዲያውቁ አጠፋቸው ዘንድ ማኅፀን የሚከፍተውን ሁሉ በአመጡልኝ ጊዜ፥ በመባቸው አረከስኋቸው።
ቍርባናችሁን በአቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በዐሳባችሁ ሁሉ ረከሳችሁ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! እኔስ እመልስላችኋለሁን? እኔ ሕያው ነኝ! አልመልስላችሁም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጎች ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? ወይስ የበኵር ልጄን ስለ በደሌ፥ የሆዴንም ፍሬ ስለ ነፍሴ ኃጢአት እሰጣለሁን?
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንዲሁ አታድርግ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአምላኮቻቸው በእሳት ስለሚያቃጥሉ አሕዛብ ለአምላኮቻቸው የሚያደርጉትን ርኩስ ነገር እግዚአብሔር ይጠላልና።
ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ላላዘዘህ ለፀሐይና ለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ ቢገኝ፥
ድንበሩም በሄኖም ልጅ ሸለቆ አጠገብ ኢየሩሳሌም ወደምትባለው ወደ ኢያቡስ ወደ ደቡብ ወገን ይወጣል፤ ድንበሩም በሰሜን በኩል በራፋይም ሸለቆ ዳር ባለው በሄኖም ሸለቆ ፊት ለፊት በባሕር በኩል ወዳለው ተራራ ራስ ላይ ይወጣል፤