ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትና ሽማግሌዎቹም ማቅ ለብሰው በግንባራቸው ተደፉ።
ኤርምያስ 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጄን በዚች ምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና ቤቶቻቸዉ፥ እርሻዎቻቸውም፥ ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሰጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ በሚኖሩት ላይ እጄን በምዘረጋበት ጊዜ፣ ዕርሻቸውና ሚስቶቻቸው ሳይቀሩ፣ ቤቶቻቸው ለሌሎች ይሆናሉ፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጄን በምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና፤ ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ፥” ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የዚህችን ምድር ሕዝብ በምቀጣበት ጊዜ ቤቶቻቸው፥ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸው ጭምር ለሌሎች ይሰጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እጄን በምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
ዳዊትም ዐይኖቹን አነሣ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በምድርና በሰማይ መካከል ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተዘርግቶ አየ። ዳዊትና ሽማግሌዎቹም ማቅ ለብሰው በግንባራቸው ተደፉ።
በሐሣር እንዳትወድቁ፥ ክብራችሁን ወዴት ትተዉታላችሁ? በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፥ አረማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
ሰው ሁሉ ክፉና በደለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመፅን ይናገራልና፥ ስለዚህ ጌታ በጐልማሶቻቸው ደስ አይለውም፤ ለሙት ልጆቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
እያንዳንዱም የክንዱን ሥጋ ይበላል፤ ምናሴ ኤፍሬምን፥ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱ በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉና። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
አንቺ እኔን ከድተሽኛል፤ እኔንም መከተል ትተሻል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ፤ ይቅርም አልላቸውም።
እነሆ በይሁዳ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ፤ እነዚያም ሴቶች፦ ባለሟሎችህ አታልለውሃል፤ አሸንፈውህማል፤ እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ከገቡ እነርሱ ከአንተ ወደ ኋላ ተመልሰዋል ይላሉ።
ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።”
እንግዲህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።”
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመለኪያውንም ገመድ ዘረጋ፤ እርስዋን ከማጥፋት እጁን አልመለሰም፤ ምሽጉና ቅጥሩ አለቀሱ፤ በአንድነትም ደከሙ።
እንዲህም በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሴይር ተራራ ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፤ እጄን እዘረጋብሃለሁ፤ ባድማና ውድማም አደርግሃለሁ።
ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ፤ ቤታቸውንም ይወርሳሉ፥ የኀያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ።
በዚያ ቀን በምሳሌ ይመስሉባችኋል፥ በጽኑ ልቅሶም ያለቅሱላችኋል፥ እነርሱም፦ ፈጽመን ጠፍተናል፥ የሕዝቤን እድል ፈንታ ይሰፍራል፥ እርሱንም የሚከለክል የለም፥ እርሻችንን ለዓመፀኞች ይከፍላል ይላሉ።
ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።