ኤርምያስ 51:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋትን ትተዋል፤ በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸውም ጠፍቶአል፤ እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ጦረኞች መዋጋት ትተዋል፤ በምሽጎቻቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኀይላቸው ተሟጥጧል፤ እንደ ሴት ሆነዋል፤ በማደሪያዎቿም እሳት ተለኵሷል፤ የደጇም መወርወሪያ ተሰብሯል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኃይላቸውም ደክሙአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፤ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መቀርቀሪያዎችዋም ተሰብረዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎን ኃያላን መዋጋትን ትተዋል በአምባዎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል፥ ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል፥ ማደሪያዎችዋም ነድደዋል መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል። |
በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከሚያወርድባቸው ፍርሀትና መንቀጥቀጥ የተነሣ ግብፃውያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ።
እነሆ፥ ሁሉም እንደ እብቅ እሳት ይቃጠላሉ፤ ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኀይል አያድኑም፤ እንደ እሳትም ፍም ይሆኑብሻል፤ በላያቸውም ትቀመጫለሽ።
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹሞችዋን፥ ኀያላኖችዋንም አሰክራለሁ፤ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰበሩ፤ ንጉሥዋና አለቃዋ በአሕዛብ መካከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢያቷም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላዩም።
የደማስቆንም ቍልፎች እሰብራለሁ፤ በአዎን ሸለቆ የሚኖሩትንም ሰዎች አጠፋለሁ፤ የካራን ሰዎች ወገኖችንም እቈራርጣለሁ፤ የሶርያ ሕዝብም ወደ ቂር ይማረካሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።