ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
ኤርምያስ 50:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጊዜዋ ደርሶአልና ሣጥኖችዋን ከፍታችሁ እንደ ዋሻ በርብሯት፤ ጨርሳችሁም አጥፏት፥ ምንም አታስቀሩላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሩቅ መጥታችሁ በርሷ ላይ ውጡ፤ ጐተራዎቿን አፈራርሱ፤ እንደ እህል ክምር ከምሯት፤ ፈጽማችሁ አጥፏት፤ ምኗም አይቅር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከየአቅጣጫው በእርሷ ላይ ኑ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፤ እንደ ተቈለለ ነዶ ከምርዋት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ ምንም ዓይነት ነገር አታስተርፉላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከየአቅጣጫው ዝመቱባት፤ እህልዋ የተከማቸበትን ጐተራ ሁሉ ክፈቱ፤ ምርኮውንም እንደ እህል ምርት ቈልሉት፤ ምንም ነገር ሳትተዉ አገሪቱን አጥፉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ውጡ፥ ጎተራዎችዋንም ክፈቱ፥ እንደ ክምርም አድርጓት ፈጽማችሁም አጥፉአት፥ አንዳችም አታስቀሩላት። |
ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር በዚህ ተራራ ላይ ዕረፍትን ይሰጠናል፤ እህልም በመንኰራኵር ጭድም በጭቃ እንደሚበራይ እንዲሁ ሞዓብ ይረገጣል።
በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበሩትን መዛግብት እሰጥሃለሁ፤ የማይታየውንም የተደበቀውን ሀብት እገልጥልሃለሁ።
በሩቅ ላሉ አሕዛብም ምልክትን ያቆማል፤ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነሆም፥ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።
ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይቀመጥባትም፤ በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
ምድርን ሁሉ የምትፈጫት መዶሻ እንዴት ደቀቀች! እንዴትስ ተሰበረች! ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት ባድማ ሆነች!
በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋታለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርስዋ አይሰበሰቡም፤ የባቢሎንም ቅጥሮች ይወድቃሉ።
አንተም፦ እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፤ አትነሣምም በል።” የኤርምያስ ቃል እስከዚህ ድረስ ነው።
ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም በጎተራም አይከቱም፤ የሰማዩ አባታችሁም ይመግባቸዋል፤ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።