Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 19:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ወጣ፤ “በብረት በትርም ይገዛቸዋል።” እርሱም ሁሉን ቻይ የሆነውን የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣ ወይን መጭመቂያ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቁጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሕዝቦችን የሚመታበት ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ በብረት በትርም ይገዛቸዋል፤ እርሱ ሁሉን የሚችለውን የእግዚአብሔር አስፈሪ ቊጣ መግለጫ የሆነውን የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 19:15
15 Referencias Cruzadas  

በብ​ረት በትር ትጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃም ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።


ከቀ​ድ​ሞም ጀምሮ የማ​ቃ​ጠያ ስፍራ ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ለች፤ ለን​ጉ​ሥም ተበ​ጅ​ታ​ለች፤ ጥል​ቅና ሰፊም አድ​ር​ጎ​አ​ታል፤ እሳ​ትና ብዙ ማገዶ ተከ​ም​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


መከሩ ደር​ሶ​አ​ልና ማጭድ ስደዱ፤ መጭ​መ​ቂ​ያ​ውም ሞል​ቶ​አ​ልና ኑ ርገጡ፤ ክፋ​ታ​ቸ​ውም በዝ​ቶ​አ​ልና መጭ​መ​ቂያ ሁሉ ፈስ​ሶ​አል።”


መጥቼም ምድርን በእርግማን እንዳልመታ እርሱ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች፥ የልጆችንም ልብ ወደ አባቶች ይመልሳል።


በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዐመፀኛ ይገለጣል፤


በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፤ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኀይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።


አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።


እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።


የቀሩትም በፈረስ ላይ ከተቀመጠው ከአፉ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ፤ ወፎችም ሁሉ ከሥጋቸው ጠገቡ።


“በጴርጋሞንም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፡ በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ያለው እንዲህ ይላል፦


እንግዲህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos