ኤርምያስ 50:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም በሬዎች ቷጋላችሁና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ ርስቴን የበዘበዛችሁ ሆይ፤ ደስ ስላላችሁና ሐሤትም ስላደረጋችሁ፣ በመስክ እንዳለች ጊደር ስለ ፈነጫችሁ፤ እንደ ድንጉላ ፈረስ ስለ አሽካካችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ፥ ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች አሽካክታችኋልና፥ |
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፥ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፤ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ፥ ይህን ስሚ፤
እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
በእርስዋም ያሉ የተቀጠሩ ሠራተኞች በእርስዋ ተቀልበው እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የጥፋታቸው ቀንና የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና ተመለሱ፤ በአንድነትም ሸሹ፤ አልቆሙምም።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
ፍሬዋን ሁሉ አድርቁባት፤ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው ደርሳለችና፥ እነሱን የሚበቀሉበት ጊዜ ደርሷልና ወዮላቸው!
ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ ጠላቶች ሁሉ መከራዬን ሰምተዋል፤ አንተ አድርገኸዋልና ደስ አላቸው፤ ስለ እርሱ የተናገርኸውን ቃል ታመጣለህ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሆናሉ።
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ! አንተና መላው ኤዶምያስ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።”
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
ኤፍሬምም ቀንበርን እንደ ለመደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአንገቱ ውበት እጫንበታለሁ፤ በኤፍሬም ላይ እጠምድበታለሁ፤ ይሁዳንም እለጕመዋለሁ፤ ያዕቆብም ለራሱ መንግሥትን ያስተካክላል።
በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኞችንም የምታስጨንቁ፥ ጌቶቻቸውንም፦ አምጡ እንጠጣ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።
በጠላት ቀን ወንድምህን ዝቅ አድርገህ ትመለከተው ዘንድ፥ በጥፋታቸውም ቀን በይሁዳ ልጆች ላይ ደስ ይልህ ዘንድ፥ በጭንቀታቸውም ቀን በትዕቢት ትናገር ዘንድ ባልተገባህ ነበር።
እግዚአብሔርም ከኢየሩሳሌም ጋር የተዋጉትን አሕዛብ ሁሉ የሚቀሥፍበት ቸነፈር ይህ ነው፣ በእግራቸው ሲቆሙ ሥጋቸው ይበሰብሳል፥ ዓይኖቻቸውም በዓይነስባቸው ውስጥ ይበሰብሳሉ፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።