Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 50:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 “እናንተ ርስቴን የበዘበዛችሁ ሆይ፤ ደስ ስላላችሁና ሐሤትም ስላደረጋችሁ፣ በመስክ እንዳለች ጊደር ስለ ፈነጫችሁ፤ እንደ ድንጉላ ፈረስ ስለ አሽካካችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የባቢሎን ሕዝብ ሆይ! ሕዝቤን፥ በመበዝበዛችሁ ደስታና ሐሴት በማድረግ ፈንጥዛችሁ ነበር፤ በመስክ ላይ እንደምትፈነጭ ጊደር ተቀናጥታችሁ፥ እንደ ሰንጋ ፈረሶችም አሽካክታችሁ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ርስ​ቴን የም​ት​በ​ዘ​ብዙ እና​ንተ ሆይ! ደስ ብሎ​አ​ች​ኋ​ልና፥ ሐሤ​ት​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ በመ​ስክ ላይም እን​ዳ​ለች ጊደር ሆና​ችሁ ተቀ​ና​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና፥ እንደ ብር​ቱ​ዎ​ችም በሬ​ዎች ቷጋ​ላ​ች​ሁና፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ፥ ደስ ብሎአችኋልና፥ ሐሤትንም አድርጋችኋልና፥ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ተቀናጥታችኋልና፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች አሽካክታችኋልና፥

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:11
32 Referencias Cruzadas  

ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።


በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም።


ሕዝቤን ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴን አርክሼው ነበር፤ አሳልፌ በእጅሽ ሰጠኋቸው፤ አንቺ ግን አልራራሽላቸውም፤ በዕድሜ በገፉት ላይ እንኳ፣ እጅግ ከባድ ቀንበር ጫንሽባቸው።


“አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤


“ግብጽ ያማረች ጊደር ናት፤ ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ ከሰሜን ይመጣባታል።


ቅጥረኞች ወታደሮቿም እንደ ሠቡ ወይፈኖች ናቸው፤ የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣ እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፤ በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።


ወፍረዋል፤ ሠብተዋልም። ክፋታቸው ገደብ የለውም፤ ወላጅ የሌላቸው ፍትሕ እንዲያገኙ አልቆሙላቸውም፤ ለድኾችም መብት አልተከራከሩም።


እንደ ተቀለበ ብርቱ ድንጉላ ፈረስ ሆኑ፤ እያንዳንዱም የሌላውን ሚስት ተከትሎ አሽካካ።


“እስራኤል አንበሶች ያሳደዱት፣ የተበተነ መንጋ ነው፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ፣ ቦጫጭቆ በላው፤ በኋላም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር፣ ዐጥንቱን ቈረጣጠመው።”


ወይፈኖቿን ሁሉ ዕረዱ፤ ወደ መታረጃም ይውረዱ! የሚቀጡበት ጊዜ፣ ቀናቸው ደርሷልና ወዮላቸው!


“ሰዎች የሥቃይ ልቅሶዬን ሰሙ፤ የሚያጽናናኝ ግን ማንም የለም፤ ጠላቶቼ ሁሉ ጭንቀቴን ሰሙ፤ አንተ ባደረግኸውም ደስ አላቸው፤ አቤቱ የተናገርሃት ቀን ትምጣ፤ እነርሱም እንደ እኔ ይሁኑ።


የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ በሆነች ጊዜ ስለ ተደሰትህ፣ እኔም እንዲሁ አደርግብሃለሁ። የሴይር ተራራ ሆይ፤ አንተና መላዋ ኤዶም ባድማ ትሆናላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’ ”


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’


ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድድ፣ እንደ ተገራች ጊደር ነው፤ በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ ቀንበርን አኖራለሁ፤ ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ ይሁዳ ያርሳል፤ ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል።


እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤


ክፉ ቀን በገጠመው ጊዜ፣ በወንድምህ ሥቃይ መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ የይሁዳ ሕዝብ ሲያዝኑ ሐሤት ማድረግ አልነበረብህም፤ በጭንቀታቸውም ቀን፣ በትዕቢት ልትናገር አይገባህም ነበር።


ሁሉንም በመንጠቆ ያወጣቸዋል፤ በመረቡ ይይዛቸዋል፤ በወጥመዱ ውስጥ ይሰበስባቸዋል፤ በዚህም ይደሰታል፤ ሐሤትም ያደርጋል።


እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የወጓትን አሕዛብ ሁሉ የሚመታበት መቅሠፍት ይህ ነው፤ ገና በእግራቸው ቆመው ሳሉ ሥጋቸው ይበሰብሳል፤ ዐይኖቻቸው በጕድጓዶቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሶቻቸውም በአፎቻቸው ውስጥ እንዳሉ ይበሰብሳሉ።


ይሹሩን ወፈረ፤ ረገጠ፤ ጠገበ፤ ሰውነቱ ደነደነ፤ ለሰለሰ፤ የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ መጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos