የይሁዳም ታላላቅ ሰዎች ካህናቱና የሀገሩም ሕዝብ በአሕዛብ ርኵሰት ሁሉ መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት አረከሱ።
ኤርምያስ 5:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ኀጢአታቸው በዝቶአልና፥ የዐመፃቸውም ብዛት ጸንቶአልና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፤ የበረሃም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፤ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰባብራቸዋል፣ የምድረ በዳ ተኵላም ይቦጫጭቃቸዋል፤ ብቅ የሚለውን ሰው ሁሉ ለመገነጣጠል፣ ነብር በከተሞቻቸው ዙሪያ ያደባል፤ ዐመፃቸው ታላቅ፣ ክሕደታቸው ብዙ ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የከዳተኝነታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኩላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ነቅቶ ይጠብቃል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ብዙ ጊዜ ዐምፀው እግዚአብሔርን ትተዋል፤ ስለዚህ ጠላቶቻቸው እንደ ዱር አንበሶች ወይም እንደ በረሓ ተኲላዎች አደጋ ይጥሉባቸዋል፤ እነዚያም ጠላቶች በከተሞቹ ላይ ሸምቀው ከዚያ የሚወጡትን ሰዎች ሁሉ እንደ ነብር ሆነው ይቦጫጭቁአቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፥ የክዳታቸውም ብዛት ጸንቶአልና ስለዚህ አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፥ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፥ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፥ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል። |
የይሁዳም ታላላቅ ሰዎች ካህናቱና የሀገሩም ሕዝብ በአሕዛብ ርኵሰት ሁሉ መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት አረከሱ።
እንዲህም አልሁ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ኀጢአታችን በራሳችን ላይ በዝቶአልና፥ በደላችንም ወደ ሰማይ ከፍ ብሎአልና አምላኬ ሆይ፥ ፊቴን ወደ አንተ አነሣ ዘንድ አፍራለሁ፤ እፈራማለሁ።
አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
ዐመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፥ ኀጢአታችንም መስክሮብናልና፥ ዐመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፥ ጽድቅንም አላወቅንምና።
አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ አንገዛልህም፤ ከእንግዲህም ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?
እንደ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፤ ከአረማውያን ሰልፍና ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ ምድራቸው ምድረ በዳ ሆናለችና።”
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
ቍስልህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።
አንበሳ ከጕድጓዱ ወጥቶአል፤ አሕዛብንም ሊያጠፋቸው የሚዘርፍ ተነሥቶአል፤ ምድርሽን ባድማ ያደርግ ዘንድ፥ ከተሞችሽንም ሰው እንዳይኖርባቸው ያፈርሳቸው ዘንድ ከስፍራው ወጥቶአል።
እነሆ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና ከዮርዳኖስ ዳር ወደ ኤታም እንደ አንበሳ ይወጣል፤ ጐልማሶችንም በእርስዋ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜን የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?”
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።
በየመንገዱ ራስ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፤ ውበትሽንም አረከስሽ፤ ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን ገለጥሽ፤ ዝሙትሽንም አበዛሽ።
በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ፥ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው።
እኔም ለኤፍሬም እንደ ነብር፥ ለይሁዳም ቤት እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁና፤ እኔም ነጥቄ እሄዳለሁ፤ እወስድማለሁ፤ የሚያድናቸውም የለም።
ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።
እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ በኀጢአተኞች ሰዎች በደል በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሥታችኋል።
ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።