Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ ነገር ግን እግሮቹ የድብ፣ አፉ ደግሞ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር፤ ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን እንዲሁም ታላቅ ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኀይሉን፥ ዙፋኑንና ትልቅ ሥልጣንን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ያየሁት አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፥ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ዘንዶው የራሱን ኀይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ሥልጣን ለአውሬው ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፥ እግሮቹም እንደ ድብ እግሮች፥ አፉም እንደ አንበሳ አፍ ነበሩ። ዘንዶውም ኃይሉንና ዙፋኑን ትልቅም ሥልጣን ሰጠው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 13:2
27 Referencias Cruzadas  

የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው፤


ያየሃቸውም ዐሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።


እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።


ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።


አምስተኛውም ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ መንግሥቱም ጨለማ ሆነች፤ ከስቃይም የተነሣ መላሶቻቸውን ያኝኩ ነበር፤


ከአ​ን​በሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እን​ዳ​ገ​ኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግ​ድ​ግዳ ላይ እን​ዳ​ስ​ደ​ገ​ፈና እባብ እንደ ነደ​ፈው ሰው ይሆ​ናል።


በውኑ ኢት​ዮ​ጵ​ያዊ መል​ኩን ወይስ ነብር ዝን​ጕ​ር​ጕ​ር​ነ​ቱን ይለ​ውጥ ዘንድ ይች​ላ​ልን? በዚያ ጊዜ ክፋ​ትን የለ​መ​ዳ​ችሁ እና​ንተ ደግሞ በጎ ለማ​ድ​ረግ ትች​ላ​ላ​ች​ሁን?


ስለ​ዚህ ኀጢ​አ​ታ​ቸው በዝ​ቶ​አ​ልና፥ የዐ​መ​ፃ​ቸ​ውም ብዛት ጸን​ቶ​አ​ልና አን​በሳ ከዱር ወጥቶ ይሰ​ብ​ራ​ቸ​ዋል፤ የበ​ረ​ሃም ተኵላ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፥ ነብ​ርም በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ ይተ​ጋል፤ ከዚ​ያም የሚ​ወጣ ሁሉ ይነ​ጠ​ቃል።


ጩኸ​ታ​ቸው እንደ አን​በሳ ነው፤ እንደ አን​በሳ ደቦ​ሎ​ችም ይቆ​ማሉ፤ ከጕ​ድ​ጓዱ እን​ደ​ሚ​ወጣ አው​ሬም ይነ​ጥ​ቃሉ፤ ይጮ​ሃሉ፤ የሚ​ድ​ንም የለም።


ዐዋቂ ሰው በትካዜ ውስጥ ይወድቃል፥ አላዋቂዎች ግን ክፉን ያስባሉ።


ዘወ​ርም ብሎ አያ​ቸው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስም ረገ​ማ​ቸው፤ ወዲ​ያ​ውም ከዱር ሁለት ድቦች ወጥ​ተው ከእ​ነ​ርሱ አርባ ሁለ​ቱን ሰባ​በ​ሩ​አ​ቸው።


ፈረሶቻቸውም ከነብር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው፥ ከማታም ተኵላ ይልቅ ጨካኞች ናቸው፣ ፈረሰኞቻቸውም ይንሳፈፋሉ፥ ከሩቅም ይመጣሉ፥ ለመብልም እንደሚቸኵል ንስር ይበርራሉ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እረኛ ከአ​ን​በሳ አፍ ሁለት እግ​ርን ወይም የጆ​ሮን ጫፍ እን​ደ​ሚ​ያ​ድን፥ እን​ዲሁ በሰ​ማ​ርያ በአ​ሕ​ዛብ ፊትና በደ​ማ​ስቆ የተ​ቀ​መ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይድ​ናሉ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እከ​ተ​ለው ዘንድ እሄ​ዳ​ለሁ፤ እርሱ ያድ​ነ​ና​ልና፤ እር​ሱም እንደ አን​በሳ ያገ​ሣል፤ የውኃ ልጆ​ችም ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


“የሰይጣን ዙፋን ባለበት የምትኖርበትን አውቃለሁ፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ ሃይማኖቴን አልካድህም።


በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios