ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
ኤርምያስ 43:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅ ምድርም ያለውን የፀሐይ ከተማ ምሰሶዎችን ይሰብራል፥ የግብፅንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽ ምድር የሚገኙትን የፀሓይ አምላክ ቤተ ጣዖት ሐውልቶች ይሰባብራል፤ የግብጽንም አማልክት ቤተ ጣዖቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል። |
ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው።
ስለ ግብፅ የተነገረ ራእይ። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፤ የግብፅም የእጆቻቸው ሥራዎች በፊቱ ይዋረዳሉ፤ የግብፃውያንም ልብ በውስጣቸው ይቀልጣል።
በዚያ ቀን አምስት የግብፅ ከተሞች በከነዓን ቋንቋ ይናገራሉ፤ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔርም ስም ይጠሩ ዘንድ ከተሞች አንድ ይሆናሉ፤ ከእነዚህም አንዲቱ የጽድቅ ከተማ ተብላ ትጠራለች።
እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ፥ ከሰማይም በታች ፈጽመው ይጥፉ ትሉአቸዋላችሁ።
በግብፅም አማልክት ቤቶች እሳትን ያነድዳል፤ ያቃጥላቸውማል፤ ይማርካቸውማል፤ እረኛም ልብሱን እንደሚቀምል እንዲሁ የግብፅን ሀገር ይቀምላታል፤ ከዚያም በሰላም ይወጣል።
በግብፅ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ፥ በሜምፎስም፥ በፋቱራም ሀገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፦
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የኖእ አሞንን፥ ፈርዖንንም፥ ግብጽንም፥ አማልክቶችዋንና ነገሥታቶችዋንም፥ ፈርዖንንና በእርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ።
ፈረሶቹ አደባባይሽን ይረግጣሉ፤ ሠራዊቶችሽንም በሾተል ይገድሏቸዋል፤ የጸና አርበኛሽንም በምድር ላይ ይጥለዋል።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶቹን አጠፋለሁ፤ ምስሎቹንም ከሜምፎስ እሽራለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በግብፅ ምድር አለቃ አይሆንም፤ በግብፅ ምድር ላይም ፍርሀትን አደርጋለሁ።