ኤርምያስ 43:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በግብጽ ምድር የሚገኙትን የፀሓይ አምላክ ቤተ ጣዖት ሐውልቶች ይሰባብራል፤ የግብጽንም አማልክት ቤተ ጣዖቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።’ ” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በግብፅ ምድርም ያለውን የፀሐይ ከተማ ምሰሶዎችን ይሰብራል፥ የግብፅንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል፥ የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል። Ver Capítulo |
ከጽዋው መጠጣት የሚገባቸው ሌሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የግብጽ ንጉሥ ከባለሟሎቹና ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር፥ የግብጽ ሕዝብና በግብጽ የሚኖሩ መጻተኞች ሁሉ፥ በዑፅ ምድር የሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ፥ በፍልስጥኤማውያን ከተሞች፥ በአስቀሎና፥ በጋዛ፥ በዔቅሮንና በአሽዶድ፥ በሌሎች ቦታዎችም የሚኖሩ የኤዶም፥ የሞአብና የዐሞን ሕዝቦች ሁሉ፥ የጢሮስና የሲዶና ነገሥታት ሁሉ፥ በሜዲትራኒያን ባሕር ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ያሉ ነገሥታት ሁሉ፥ የደዳን፥ የቴማና የቡዝ ከተሞች ሁሉ፥ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የሚላጩ ሕዝቦች ሁሉ፥ የዐረብ አገር ነገሥታት ሁሉ፥ በበረሓ የሚኖሩ ነገዶች ነገሥታት ሁሉ፥ የዘምሪ፥ የዔላምና የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፥ ሌሎችም በስተሰሜን በኩል በሩቅና በቅርብ ያሉ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው። በምድር ላይ የሚኖሩት ሕዝብ ሁሉ፥ ከዚህ ጽዋ ይጠጣሉ፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ከዚህ ጽዋ መጠጣት ይኖርበታል።