La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 39:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ግን አን​ዳች ከሌ​ላ​ቸው ከሕ​ዝቡ ድሆች ከፊ​ሎ​ቹን በይ​ሁዳ ሀገር ተዋ​ቸው፤ የወ​ይ​ኑን ቦታና እር​ሻ​ው​ንም በዚያ ጊዜ ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንብረት ያልነበራቸውን ድኾች ግን የክብር ዘበኞች አዛዥ ናቡዘረዳን፣ በይሁዳ ምድር ተዋቸው፤ በዚያ ጊዜም የወይን አትክልት ቦታና የዕርሻ መሬት ሰጣቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ምንም የሌላቸውን አንዳንድ ድሆች በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ በዚያው ጊዜም የወይኑን ቦታዎችና እርሻዎችን ሰጣቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው፥ የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያን ጊዜ ሰጣቸው።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 39:10
8 Referencias Cruzadas  

የአ​በ​ዛ​ዎ​ችም አለቃ ከሀ​ገሩ ድሆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ሰው ከላ​ሞቹ አን​ዲት ጊደ​ር​ንና ሁለት በጎ​ችን ያሳ​ድ​ጋል፤ የአ​ን​ዲት በግ ወተ​ትም ሁለት ሰዎ​ችን ያጠ​ግ​ባል።


እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚ​መ​ጡት ከለ​ዳ​ው​ያን ፊት እቆም ዘንድ በመ​ሴፋ እኖ​ራ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ወይ​ኑ​ንና ፍሬ​ውን፥ ዘይ​ቱ​ንም አከ​ማቹ፤ በየ​ዕ​ቃ​ች​ሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያ​ዛ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ ተቀ​መጡ።”


በየ​ሜ​ዳው የነ​በ​ሩት የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችና ሰዎ​ቻ​ቸው ሁሉ የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን በሀ​ገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ች​ንም፥ ወደ ባቢ​ሎን ያል​ተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም የም​ድ​ርን ድሆች እን​ዳ​ስ​ጠ​በቀ በሰሙ ጊዜ፥


ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንም፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሴቶች ልጆች፥ የአ​ዛ​ዦ​ችም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሳ​ፋን ልጅ ከአ​ኪ​ቃም ልጅ ከጎ​ዶ​ል​ያስ ጋር የተ​ዋ​ቸ​ውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስ​ንና የኔ​ር​ዩን ልጅ ባሮ​ክ​ንም ወሰዱ።


የአ​ዛ​ዦ​ቹም አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ከሀ​ገሩ ድኆች ወይን ተካ​ዮ​ችና አራ​ሾች እን​ዲ​ሆኑ አስ​ቀረ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦


እኔም ለእርድ የሚሆኑትን በጎች፥ የመንጋውን ችግረኞች ጠበቅሁ። ሁለት በትሮችንም ወሰድሁ፣ የአንዲቱን ስም ውበት የሁለተኛይቱንም ስም ማሰሪያ ብዬ ጠራሁ፣ መንጋውንም ጠበቅሁ።