Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 39:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንን ስለ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል አዘ​ዘው፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በክብር ዘበኞቹ አዛዥ በናቡዘረዳን በኩል ስለ ኤርምያስ እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ በዘበኞቹ አለቃ በናቡዘረዳን በኩል እንዲህ ሲል ትእዛዝን ሰጠ፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ናቡከደነፆር የክብር ዘብ አዛዡን ናቡዛርዳንን እንዲህ ሲል አዘዘው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11-12 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ፦ ውሰደውና በመልካም ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ክፉን ነገር አታድርግበት ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 39:11
12 Referencias Cruzadas  

የመቶ አለ​ቃ​ው​ንም ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ጠ​ብ​ቀው፥ በሰፊ ቦታም እን​ዲ​ያ​ኖ​ረው፥ እን​ዳ​ያ​ጠ​ብ​በ​ትም፥ ሊያ​ገ​ለ​ግ​ሉት በመጡ ጊዜም ከወ​ዳ​ጆቹ አን​ዱን ስንኳ እን​ዳ​ይ​ከ​ለ​ክ​ል​በት አዘዘ።


ከክፉ ሰዎ​ችም እጅ እታ​ደ​ግ​ሃ​ለሁ፤ ከጨ​ካ​ኞ​ችም ጡጫ እቤ​ዥ​ሃ​ለሁ።


እር​ሱም ሆነ፥ አገ​ል​ጋ​ዮቹ፥ የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ በነ​ቢዩ በኤ​ር​ም​ያስ እጅ የተ​ና​ገ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።


አቤቱ! በመ​ከ​ራ​ቸ​ውና በጭ​ን​ቃ​ቸው ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ስለ እነ​ርሱ በጎ ነገር በአ​ንተ ፊት የቆ​ምሁ ባል​ሆን ይህ ለእ​ነ​ርሱ መከ​ና​ወን ይሁን።


ስድ​ስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድ​ን​ሃል፥ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ ክፋት አት​ነ​ካ​ህም።


በጦ​ር​ነት ይጠ​ፋሉ፤ ደካ​ማ​ውም ከኀ​ያሉ እጅ ያመ​ል​ጣል።


ለም​ስ​ኪ​ኑ ተስፋ አለ​ውና፤ የዐ​መ​ጸ​ኛም አፍ ይዘ​ጋ​ልና።


እኔ አድ​ንህ ዘንድ ከአ​ንተ ጋራ ነኝና ከፊ​ታ​ቸው የተ​ነሣ አት​ፍራ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።


ወደ ባቢ​ሎን በተ​ማ​ረ​ኩት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች መካ​ከል የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን በሰ​ን​ሰ​ለት አስሮ በወ​ሰ​ደው ጊዜ ከራማ ከለ​ቀ​ቀው በኋላ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው።


አሁ​ንም እነሆ በእ​ጅህ ካለ​ችው ሰን​ሰ​ለት ዛሬ ፈታ​ሁህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ቢታ​ይህ፥ ና፤ እኔም በመ​ል​ካም አይ​ሃ​ለሁ፤ ከእኔ ጋር ወደ ባቢ​ሎን መም​ጣት መል​ካም መስሎ ባይ​ታ​ይህ ግን፥ ተቀ​መጥ፤ ተመ​ል​ከት፥ እነሆ፥ ሀገ​ሪቱ ሁሉ በፊ​ትህ ናት፤ ትሄድ ዘንድ መል​ካም መስሎ በሚ​ታ​ይ​ህና ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኝ​ህም ስፍራ ተቀ​መጥ።”


በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በዐ​ሥራ ዘጠ​ነ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ፊት የሚ​ቆ​መው የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios