ኤርምያስ 38:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም ሴዴቅያስን፥ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች፤ ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም፥ ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፤ “የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለባቢሎን ንጉሥ የጦር መኰንኖች እጅህን ብትሰጥ፣ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ አትቃጠልም፤ አንተና ቤተ ሰብህም በሕይወት ትኖራላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ሴዴቅያስን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች በእርግጥ ብትወጣ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፤ አንተም ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያለውን ሁሉ እንዲህ ብዬ ነገርኩት፦ “የባቢሎን ንጉሥ ለላካቸው ባለ ሥልጣኖች እጅህን ብትሰጥ ሕይወትህ ትተርፋለች፤ ይህችም ከተማ ከመቃጠል ትድናለች፤ አንተና ቤተሰብህም ሁሉ ከጥፋት ትድናላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም ሴዴቅያስን፦ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፥ ነፍስህ በሕይወት ትኖራለች ይህችም ከተማ በእሳት አትቃጠልም፥ አንተም ቤትህም በሕይወት ትኖራላችሁ። |
የይሁዳም ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፥ ከብላቴኖቹም፥ ከአለቆቹም፥ ከጃንደረቦቹም ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ያዘው።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ከፍ አደረገው፤ ከወህኒ ቤትም አወጣው፤
ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፤ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው ይባል ዘንድ ስምህ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሁን፤ የአገልጋይህም የዳዊት ቤት በፊትህ የጸና ይሁን።
ስለ ምርኮኞቹም መተላለፍ የእስራኤልን አምላክ ቃል የሚፈሩ ሁሉ ወደ እኔ ተሰበሰቡ፤ እኔም እስከ ሠርክ መሥዋዕት ድረስ ዐዝኜ ተቀመጥሁ።
ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህን ቃል ሁሉ ተናገርሁ፥ “ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ለእርሱና ለሕዝቡም ተገዙላቸው በሕይወትም ኑሩ።
“ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከንደነፆር የማይገዛውን፥ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በዚች ከተማ የሚቀመጥ በሰይፍና በራብ፥ በቸነፈርም ይሞታል፤ ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል፤ ነፍሱም እንደ ምርኮ ትሆንለታለች፤ በሕይወትም ይኖራል።
የባቢሎንም ንጉሥ አለቆች ሁሉ፥ ማርጋናሳር፥ ሳማጎት፥ ናቡሳኮር፥ ናቡሰሪስ፥ ናግራጎስናሴር፥ ረብማግ፥ ኔርጋል ሴሪአጼር፥ ከቀሩት ከባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው እንዲህ ብሎ ማለ፥ “ለከለዳውያን ትገዙ ዘንድ አትፍሩ፤ በምድር ተቀመጡ፤ ለባቢሎንም ንጉሥ ተገዙ፤ መልካምም ይሆንላችኋል።
“አሁንም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከይሁዳ ወገን መካከል ቅሬታ እንዳይቀርላችሁ፥ ወንድንና ሴትን፥ ብላቴናንና የሚጠባ ሕፃንን ከመካከላችሁ ታጠፉ ዘንድ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ?