Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 5:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ስለ​ዚህ ከደ​ማ​ስቆ ወደ​ዚያ አስ​ማ​ር​ካ​ች​ኋ​ለሁ” ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የተ​ባለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ስለዚህ ከደማስቆ ማዶ እንድትጋዙ አደርጋለሁ፤” ይላል ስሙ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር የሆነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ስለዚህ ከደማስቆ ባሻገር አስማርኬ አፈልሳችኋለሁ፥” ይላል ጌታ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ የሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከደማስቆ ወዲያ ርቃችሁ እንድትሰደዱ አደርጋለሁ።” ይህን የተናገርኩ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ስለዚህ ከደማስቆ ወደዚያ አስማርካችኋለሁ፥ ይላል ስሙ የሠራዊት አምላክ የተባለ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 5:27
10 Referencias Cruzadas  

በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በፋ​ቁሔ ዘመን የአ​ሶር ንጉሥ ቴል​ጌ​ል​ቴ​ል​ፌ​ል​ሶር መጣ፤ ኢዮ​ንና አቤ​ል​ቤ​ት​መ​ዓ​ካን፥ ያኖ​ዋ​ንም፥ ቃዴ​ስ​ንና አሶ​ር​ንም፥ ገለ​ዓ​ድ​ንና ገሊ​ላ​ንም፥ የን​ፍ​ታ​ሌ​ም​ንም ሀገር ሁሉ ወሰደ፤ ወደ አሶ​ርም አፈ​ለ​ሳ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


ኤር​ም​ያ​ስም ሴዴ​ቅ​ያ​ስን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ብት​ወጣ፥ ነፍ​ስህ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለች፤ ይህ​ችም ከተማ በእ​ሳት አት​ቃ​ጠ​ልም፤ አን​ተም፥ ቤት​ህም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


እነሆ ነጐ​ድ​ጓ​ድን የሚ​ያ​ጸና፥ ነፋ​ስ​ንም የፈ​ጠረ፥ የመ​ሢ​ሕን ነገር ለሰው የሚ​ነ​ግር፥ ንጋ​ትን ጭጋግ የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ከፍ​ታ​ዎች ላይ የሚ​ረ​ግጥ፥ ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ።”


ለራ​ሳ​ች​ሁም የሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውን ምስ​ሎች፥ የሞ​ሎ​ክን ድን​ኳ​ንና የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የሬ​ፋ​ንን ኮከብ አነ​ሣ​ችሁ።


ጽዮ​ንን ለሚ​ንቁ፥ በሰ​ማ​ር​ያም ተራራ ለሚ​ታ​መኑ ሰዎች ወዮ​ላ​ቸው፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን አለ​ቆች ለቀ​ሙ​አ​ቸው።


ስለ​ዚህ ከአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸው አስ​ቀ​ድ​መው ይማ​ረ​ካሉ፤ ሯጮች የሚ​ሆኑ የኤ​ፍ​ሬም ፈረ​ሶ​ችም ያል​ቃሉ።


ነገር ግን የሞ​ሎ​ህን ድን​ኳን አነ​ሣ​ችሁ፤ ሬፋን የሚ​ባ​ለ​ው​ንም ኮከብ አመ​ለ​ካ​ችሁ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ዘንድ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን አበ​ጃ​ችሁ፤ እኔም ወደ ባቢ​ሎን እን​ድ​ት​ማ​ረኩ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ።’


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos