ኤርምያስ 38:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፥ “አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡ ሴዴቅያስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ልኮ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስተኛው በር አስመጣውና፤ “አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በጌታ ቤት ወደነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፦ “እኔ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ ወደ እርሱ አስጠራኝና በቤተ መቅደሱ ሦስተኛ በር አጠገብ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነው፤ አንዳች ነገር ሳትደብቅ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፥ ንጉሡም ኤርምያስን፦ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፥ ምንም አትሸሽገኝ አለው። |
የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
በእግዚአብሔርም ቤት የዙፋኑን መሠረት ሠራ፤ ስለ አሦርም ንጉሥ በውጭ ያለውን የንጉሡን መግቢያ ወደ እግዚአብሔር ቤት አዞረው።
ነቢዩ ሚክያስም፥ “ውጣ፤ ተከናወን፤ በእጅህም አልፈው ይሰጣሉ” አለ። ንጉሡም፥ “በእግዚአብሔር ስም ከእውነት በቀር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ አምልሃለሁ?” አለው።
አቤቱ! በመከራቸውና በጭንቃቸው ጊዜ በጠላቶቻቸው ዘንድ ስለ እነርሱ በጎ ነገር በአንተ ፊት የቆምሁ ባልሆን ይህ ለእነርሱ መከናወን ይሁን።
ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈይታ ጠየቀው። ኤርምያስም፥ “አዎን አለ፤ ደግሞም በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ” አለው።
እናንተ፦ ሰለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፤ አምላካችንም እግዚአብሔር የሚናገርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እናደርገዋለን ብላችሁ ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ልካችሁኝ ነበርና ራሳችሁን አታልላችኋል።