Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 38:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ንጉሡ ሴዴቅያስ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ልኮ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሦስተኛው በር አስመጣውና፤ “አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በጌታ ቤት ወደነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፦ “እኔ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ ወደ እርሱ አስጠራኝና በቤተ መቅደሱ ሦስተኛ በር አጠገብ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነው፤ አንዳች ነገር ሳትደብቅ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ነበ​ረው ወደ ሦስ​ተ​ኛው መግ​ቢያ ወደ እርሱ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን አስ​መ​ጣው፤ ንጉ​ሡም ኤር​ም​ያ​ስን፥ “አን​ዲት ነገር እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ምንም አት​ሸ​ሽ​ገኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፥ ንጉሡም ኤርምያስን፦ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፥ ምንም አትሸሽገኝ አለው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 38:14
11 Referencias Cruzadas  

ከዚያም ንጉሡ ሴቲቱን፣ “እኔም ለምጠይቅሽ ነገር አንቺም መልሱን አትደብቂኝ” አላት። ሴቲቱም፣ “ንጉሥ ጌታዬ፤ ዕሺ ይናገር” አለችው።


እንዲሁም በገበታው ላይ የሚቀርበውን መብል፣ የሹማምቱን አቀማመጥ፣ የአስተናባሪዎቹን አቋቋምና የደንብ ልብሳቸውን፣ ጠጅ አሳላፊዎቹን፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ያቀረባቸውን የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ባየች ጊዜ እጅግ ተደነቀች።


ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ የማምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።


የአሦርንም ንጉሥ ለማስደሰት ሲል፣ በዕለተ ሰንበት ንጉሣዊ ዙፋን እንዲዘረጋበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ የተሠራውን ከፍ ያለ ስፍራና ነገሥታቱ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገቡበትን በውጭ ያለውን መግቢያ አነሣ።


ንጉሡም፣ “ከእውነት በቀር ምንም ነገር በእግዚአብሔር ስም እንዳትነግረኝ የማምልህ ስንት ጊዜ ነው?” አለው።


እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤ በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።


ከዚያም በኋላ ንጉሡ ሴዴቅያስ ላከበትና ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣው፤ ለብቻውም ወስዶ፣ “ከእግዚአብሔር የመጣ ቃል አለህ?” በማለት ጠየቀው። ኤርምያስም፣ “አዎን አለ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ዐልፈህ ትሰጣለህ” አለው።


‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት ፈጸማችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos