በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
ኤርምያስ 35:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘለዓለም አይታጣም፥” ይላል የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን የሚያገለግለኝ ሰው ለዘላለም አይታጣም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘለዓለም ፈጽሞ አይታጣም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ከዘሩ ምንጊዜም እኔን የሚያገለግል ሰው አይጠፋም።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ በፊቴ የሚቆም ሰው ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘላለም አይታጣም። |
በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም፥ ልቤ ወደዚህ ሕዝብ አያዘነብልም፤ እነዚህን ሕዝቦች ከፊቴ አባርራቸው፤ ይውጡ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ብትመለስ እመልስሃለሁ፤ በፊቴም ትቆማለህ፤ የከበረውንም ከተዋረደው ብትለይ እንደ አፌ ትሆናለህ፤ እነርሱ ወደ አንተ ይመለሳሉ፤ አንተ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
እነሆ እኔም ወደ እኛ በሚመጡት ከለዳውያን ፊት እቆም ዘንድ በመሴፋ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይኑንና ፍሬውን፥ ዘይቱንም አከማቹ፤ በየዕቃችሁም ውስጥ ክተቱ፤ በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ተቀመጡ።”