ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘካራ የምትባል የኔሬያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበረች፤ አባቶቹም እንዳደረጉ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። 5 ‘ሀ’ በእነዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገዛለት። ከእርሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግዚአብሔርም የከለዳውያንንና የሶርያውያንን፥ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ልጆችና የሰማርያን አደጋ ጣዮች ላከበት፤ ከዚህም በኋላ በአገልጋዮቹ በነቢያት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለሠራቸው ኀጢአቶችና ኢዮአቄም ስላፈሰሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየሩሳሌምንም በንጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግዚአብሔርም ሊያጠፋቸው አልፈለገም ነበር።