ኤርምያስ 30:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የሚያስፈራ ድምፅ ትሰማላችሁ፤ ፍርሀት ነው እንጂ ሰላም አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቷል፤ ሰላምም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላልና፦ የሽብር ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰላም ሳይሆን የመሸበርና የመርበድበድ ድምፅ ይሰማል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፥ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም። |
ወራዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥተዋል፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበላልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።
ፈርተው ወደ ኋላ ሲመለሱ፥ ኀያላኖቻቸውም ሲደክሙ፥ ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙሪያቸውም ይከቡአቸዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
የፈረሶቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠራዊቱ ፈረሶች ሩጫ ድምፅ የተነሣም ምድር በመላዋ ተንቀጠቀጠች፤ መጥተውም ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማዪቱንና የተቀመጡባትንም በሉ።
እነሆ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የወገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተቀረፁ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱነትስ ያስቈጡኝ ስለ ምንድን ነው?
ምድርን ትተናልና፥ ቤቶቻችንንም ጥለን ሄደናልና እንዴት ጐሰቈልን! እንዴት አፈርን! የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።