አንተ ግን አቤቱ! ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውንም ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፤ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።”
ኤርምያስ 26:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱና ነቢያተ ሐሰትም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፥ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሮአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው” ብለው ተናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱና ነቢያቱም ለባለሥልጣኖቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “በጆሯችሁ እንደ ሰማችሁት ይህ ሰው በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ስለ ተናገረ ሞት ይገባዋል” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ “በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁት በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግሯልና ይህ ሰው ሞት ይገባዋል” ብለው ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱና ነቢያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ፦ በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው ብለው ተናገሩ። |
አንተ ግን አቤቱ! ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ የመከሩትን ምክር ሁሉ ታውቃለህ፤ በደላቸውንም ይቅር አትበል፤ ኀጢአታቸውንም ከፊትህ አትደምስስ፤ በፊትህም ይውደቁ፤ በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።”
አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያተ ሐሰት፥ “ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሞት አይገባውም” አሉ።
አለቆቹም ንጉሡን፥ “ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚያች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ፥ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል፤ ለዚህ ሕዝብ ክፋትን እንጂ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
አይሁድም መልሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋችንም ሊሞት ይገባል፤ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጎአልና” አሉት።
ከጳውሎስም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ “ይህ በሕይወት ሊኖር አይገባውምና እንዲህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው” እያሉ ጮሁ።
ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን ቃል በስሜ የሚናገር ነቢይ፥ በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይም፥ እርሱ ይገደል።
የከተማዉም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበዓልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቈርጦአልና ይገደል ዘንድ ልጅህን አምጣ” አሉት።