ኤርምያስ 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እግዚአብሔር እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋራ ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ እንጂ አያሸንፉም፤ ክፉኛ ይዋረዳሉ እንጂ አይሳካላቸውም፤ ውርደታቸውም ከቶ አይረሳም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ግን እንደ ጀግና ወታደር ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ በመደናቀፍ ኀይል አጥተው ይወድቃሉ። በሚወድቁበትም ጊዜ ክፉኛ ይዋረዳሉ፤ ውርደታቸውም ለረጅም ጊዜ ይታወሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያልና እንደ ጨካኝ ከእኔ ጋር ነው፥ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፥ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘላለምም በማይረሳ ጕስቍልና ይጐሰቍላሉ። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ያዕቆብ ሆይ፥ አትፍራ፤ በቍጥር ጥቂት የነበርህ እስራኤል ሆይ፥ እኔ እረዳሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
እነሆ በምድሪቱ ሁሉ ላይ፥ በይሁዳም ነገሥታት በአለቆችዋና በካህናቷ ላይ፥ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገች ከተማ፥ እንደ ብረትም ዓምድ፥ እንደ ናስም ቅጥር ዛሬ አድርጌሃለሁ።
አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤ ከሚያሳድዱኝም አድነኝ እንጂ፥ አትታገሣቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደቡኝ አስብ።
አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው።
በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይወስዳቸዋል፤ ወዳጆችሽም ተማርከው ይሄዳሉ፤ በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ፤ በወዳጆችሽም ፊት ቷረጃለሽ።
ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕረትን ታደርጋለህ፤ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ብብት ትመልሳለህ።