አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገዋል፤ እርሱንም ረስተዋል፤ ፊታቸውንም ከእግዚአብሔር ቤት መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም አዙረዋል፤
ኤርምያስ 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግንዱን፥ “አንተ አባቴ ነህ፤ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ” ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፥ “ተነሥተህ አድነን ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛፉን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ’ ድንጋዩንም፣ ‘አንተ ወለድኸኝ’ አሉ፤ ፊታቸውን ሳይሆን፣ ጀርባቸውን ሰጥተውኛልና፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ‘መጥተህ አድነን’ ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግንዱን፦ ‘አንተ አባቴ ነህ፤’ ድንጋዩንም፦ ‘አንቺ ወለድሺኝ’ ይላሉ፤ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ‘ተነሥተህ አድነን’ ይላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዛፍን ‘አባታችን’፥ አለትንም ‘የወለድሽን እናታችን’ የምትሉ ሁሉ ኀፍረት ይደርስባችኋል፤ ይህም የሚሆነው ወደ እኔ በመመለስ ፈንታ ከእኔ ስለ ራቃችሁ ነው፤ መከራ ሲደርስባችሁ ግን መጥቼ እንዳድናችሁ ትጠይቁኛላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግንዱን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ድንጋዩንም፦ አንተ ወለድኸኝ ይላሉ፥ ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ፥ በመከራቸው ጊዜ ግን፦ ተነሥተህ አድነን ይላሉ። |
አባቶቻችን ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አድርገዋል፤ እርሱንም ረስተዋል፤ ፊታቸውንም ከእግዚአብሔር ቤት መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም አዙረዋል፤
በምድረ በዳ ባሉ ውኃዎች ተዘረጋች፤ በሰውነቷም ምኞት ትወሰዳለች፤ ይይዟታል፤ የሚመልሳት ግን የለም፤ የሚሹአትም አይደክሙም፤ በተዋረደችበትም ጊዜ ያገኙአታል።
አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፥ በዝግባ ዛፍም ውስጥ የምታለቅሺ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ትጨነቂያለሽ!
ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ፤ እኔም በማለዳ ተነሥቼ ሳስተምራቸው ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አልሰሙም።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፥ “ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የማሴውን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።
እንዲህም አሉት፥ “እባክህ ልመናችን በፊትህ ትድረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነዚህም ቅሬታዎች ሁሉ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ ዐይኖችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀርተናልና።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ኀጢአትሽን ተሸከሚ።”
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ፥ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።
ሕዝቤ በዝሙት መንፈስ ስተዋልና ከአምላካቸውም ርቀው አመንዝረዋልና በትርን ይጠይቃሉ፤ በትሩም ይመልስላቸዋል።