ኤርምያስ 17:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳዳጆች ይፈሩ፤ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፤ በሁለት እጥፍ ጥፋት ቀጥቅጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሳዳጆቼ ይፈሩ፤ እኔን ግን ከዕፍረት ጠብቀኝ፤ እነርሱ ይደንግጡ፤ እኔን ግን ከድንጋጤ ሰውረኝ፤ ክፉ ቀን አምጣባቸው፤ በዕጥፍ ድርብ ጥፋት አጥፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፤ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፤ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! በሚያሳድዱኝ ሁሉ ላይ ኀፍረትን አምጣባቸው፤ እኔን ግን አታሳፍረኝ፤ እነርሱ እንዲሸበሩ አድርግ፤ እኔን ግን አታስደንግጠኝ፤ ተሰባብረው እስኪደቁ ድረስ ደጋግመህ አጥፋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳዳጆቼ ይፈሩ፥ እኔ ግን አልፈር፥ እነርሱ ይደንግጡ፥ እኔ ግን አልደንግጥ፥ ክፉንም ቀን አምጣባቸው፥ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው። |
አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር።
ኵላሊትንና ልብን የምትፈትን፥ በቅንም የምትፈርድ እግዚአብሔር ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ከእነርሱ ፍረድልኝ።
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
“እንደዚህም ብለህ ትነግራቸዋለህ፦ የወገኔ ልጅ ድንግሊቱ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ዐይኖቻችሁ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባን ያፍስሱ።
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
አቤቱ! የእስራኤል ተስፋ ሆይ! የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ፤ ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይጻፋሉ።
እኔም አንተን ተከትዬ አልደከምሁም፥ የሰውንም ቀን አልተመኘሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣውም በፊትህ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ሂድ፤ የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት በሕዝብህ ልጆች በር በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።”
እግዚአብሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆች ይሰናከላሉ፤ አያሸንፉም፤ ለዘለዓለምም የማይረሳ ጕስቍልናቸውን አላወቁምና ፈጽመው አፈሩ።