ኤርምያስ 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ ፍላጎት ሄዳችኋል፤ እኔንም አልሰማችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም ደግሞ ከአባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አድርጋችኋል፤ እያንዳንዳችሁ እኔን በመታዘዝ ፈንታ የልባችሁን ክፋት ምን ያህል በእልኸኝነት እንደምትከተሉ ተመልከቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ደግሞ ከቀድሞ አባቶቻችሁ የባሰ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ሁላችሁም እልኸኞችና ዐመፀኞች ሆናችሁ፤ ለእኔም አትታዘዙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፥ እነሆም፥ ሁላችሁ እንደ ክፉ ልባችሁ እልከኝነት ሄዳችኋል እኔንም አልሰማችሁም። |
እግዚአብሔር አምላክም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፥ “ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰዎች ሥራ አልረግምም፤ በሰው ልብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖራል፤ ደግሞም ከዚህ ቀደም እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደገና አልመታም።
የበደለ ከጥንት ጀምሮ ከዚያም በፊት ኀጢአትን አድርጓል፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት ደኅንነት እንዲሆን አውቃለሁና፤
ከፀሓይ በታች የተደረገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸው ሳሉ ሁከት በልባቸው አለ፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።
ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፥ በክፉ ልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፥ ያገለግሏቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት ተከትለው የሚሄዱ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንደማትረባ እንደዚች መታጠቂያ ይሆናሉ።
እነርሱ ግን፥ “እንጨክናለን፤ ክዳታችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም ክፉ ልባችንን ደስ የሚያሰኛትን እናደርጋለን” አሉ።
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ፤ ወደፊትም ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ከአደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
ስለዚህ ለእስራኤል ቤት እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ በአባቶቻችሁ ኀጢአት ረከሳችሁ፤ አመነዘራችሁ፤ ርኵሰታቸውንም ተከተላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ከንቱ ነገር አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።
“የዚህንም ርግማን ቃሎች በሰማችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስንፍና በማድረግ ሄጃለሁና ይቅር ይለኛል’ የሚል ቢኖር የበደለኛ ፍዳ ካልበደለ ጋር እንዳይተካከል፥
በራስህ የማልህላቸውን አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን፥ ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ልበ ደንዳናነት፥ ክፋቱንም፥ ኀጢአቱንም አትመልከት፤
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ዕወቁ፤ ከእናንተ ባንዱ ላይ ስንኳ ሃይማኖት የጐደለውና ተጠራጣሪ፥ ከሕያው እግዚአብሔር የሚለያችሁ ክፉ ልብ አይኑር።
መስፍኑ ግን ከሞተ በኋላ ዳግመኛ ተመልሰው ከአባቶቻቸው ይልቅ እጅግ ይበድሉ፤ ነበር፤ ሂደውም ሌሎች አማልክትን ተከትለው ያመልኳቸው ነበር፤ ይሰግዱላቸውም ነበር፤ ክፋታቸውንም አይተዉም ነበር፤ ከክፉ መንገዳቸውም አይመለሱም ነበር።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።