ኤርምያስ 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኢየሩሳሌም ሆይ! የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኢየሩሳሌም ሆይ፤ የሚራራልሽ ማን ነው? ማንስ ያለቅስልሻል? ደኅንነትሽንስ ማን ጐራ ብሎ ይጠይቃል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ኢየሩሳሌም ሆይ! የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ቆም ብሎ የሚጠይቅ ማነ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ማን ይራራላችኋል? የሚያዝንላችሁስ ማን ነው? ለአንድ አፍታ ቆም ብሎ ስለ ሁኔታችሁስ የሚጠይቅ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሩሳሌም ሆይ፥ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ፈቀቅ የሚል ማነ ነው? |
አሁንም እነዚህ ሁለቱ ይጠብቁሻል፤ ማን ያስተዛዝንሻል? እነርሱም ጥፋትና ውድቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንግዲህ የሚያጽናናሽ ማን ነው?
ሰውንና ወንድሙን፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ እበትናቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራላቸውም፤ አላዝንላቸውም፤ አልምራቸውምም።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰላሜን፥ ቸርነቴንና ምሕረቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና ልቅሶ ወዳለበት ቤት አትግባ፤ ታለቅስና ታዝንም ዘንድ አትሂድ።
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና አገልጋዮቹን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ፥ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትን ሕዝቡንም በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ፥ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፤ አይራራላቸውም፤ አይምራቸውም።”
ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፤ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ረከሰች ሆናለች።