ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
ኤርምያስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኬልቅያስ ልጅ፣ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ አባቱ በብንያም አገር በዓናቶት ከሚገኙት ካህናት አንዱ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በብንያም ነገድ ርስት ውስጥ በምትገኝ ዐናቶት በምትባል መንደር ከሚኖሩ ካህናት አንዱ የሆነው የሕልቅያ ልጅ ኤርምያስ የተናገረው ቃል የሚከተለው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በብንያም አገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት የሆነ የኬልቅያስ ልጅ የኤርምያስ ቃል። |
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
ኤርምያስም ለንጉሡ ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።
በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ከነቢዩ ከኤርምያስ ፊት፥ ከእግዚአብሔርም ቃል የተነሣ አላፈረም።
በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፥ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አገኘች።
በኤርምያስ አፍ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል ከተፈጸመ በኋላ በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ ደግሞም በጽሕፈት እንዲህ አለ፦
በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
ስለዚህም፥ “በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር” ብለው ነፍሴን ስለሚሹ ስለ አናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
የእግዚአብሔር ቃል በከለዳውያን ሀገር በኮቦር ወንዝ ላይ ወደ ቡዝ ልጅ ወደ ካህኑ ወደ ሕዝቅኤል መጣ። የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ በእኔ ላይ ሆነች፤
በቴቁሔ በላም ጠባቂዎች መካከል የነበረ አሞጽ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከሆነበት ከሁለት ዓመት በፊት ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ቃል ይህ ነው።
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል ዐምፆብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም” አለ።