Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 36:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በአ​ም​ላ​ኩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ከነ​ቢዩ ከኤ​ር​ም​ያስ ፊት፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የተ​ነሣ አላ​ፈ​ረም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊትም ራሱን ዝቅ አላደረገም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ ከጌታም አንደበት የመጣውን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላወረደም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እርሱም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ የእግዚአብሔርን ቃል የተናገረውን ነቢዩን ኤርምያስን በትሕትና አላዳመጠውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ በእግዚአብሔርም አፍ በተናገረው በነቢዩ በኤርሚያስ ፊት ራሱን አላወረደም።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 36:12
16 Referencias Cruzadas  

ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰው​ነ​ቱን አዋ​ረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ዘመን ቍጣ​ውን አላ​መ​ጣ​ባ​ቸ​ውም።


በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


አሁ​ንም አቤቱ፥ የጻ​ድ​ቃን አም​ላ​ካ​ቸው አንተ ነህ። ንስ​ሓን የፈ​ጠ​ርህ ለጻ​ድቅ ሰው አይ​ደ​ለ​ምና፥ አን​ተን ላል​በ​ደሉ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አይ​ደ​ለ​ምና፤ ነገር ግን የእ​ኔን የኃ​ጥ​ኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመ​ለስ።


አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ፈጽሜ በደ​ልሁ፤ ኀጢ​አ​ቴ​ንም አም​ና​ለሁ።


ኢዮ​ስ​ያስ ግን ይዋ​ጋው ዘንድ ተጽ​ናና እንጂ ፊቱን ከእ​ርሱ አል​መ​ለ​ሰም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን የኒ​ካ​ዑን ቃል አል​ሰ​ማም፤ በመ​ጊ​ዶ​ንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


በብ​ን​ያም ሀገር በዓ​ና​ቶት ከነ​በሩ ካህ​ናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬል​ቅ​ያስ ልጅ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል።


ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ርሁ፥ “ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ለእ​ር​ሱና ለሕ​ዝ​ቡም ተገ​ዙ​ላ​ቸው በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ።


ኢዮ​አ​ቄ​ምም እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።


በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።


እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኀይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos