ኢሳይያስ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዳዊት ቤትም፥ “አራም ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል” የሚል ወሬ ተነገረ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ ተናወጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዳዊት ቤት፣ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዳዊት ቤት፤ “ሶርያና ኤፍሬም ተባብረዋል” የሚል ወሬ በደረሰ ጊዜ፤ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ የአካዝና የሕዝቡ ልብ እንዲሁ ተናወጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶርያ ከእስራኤል መንግሥት ጋር በመተባበር የጦር ቃል ኪዳን መግባትዋን የይሁዳ ንጉሥ በሰማ ጊዜ እርሱና ሕዝቡ ደንግጠው ልባቸው በነፋስ እንደ ተመታ ዛፍ ተናወጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዳዊትም ቤት፦ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል የሚል ወሬ ተነገረ፥ የእርሱም ልብ የሕዝቡ ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ። |
እስራኤልም ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ባዩ ጊዜ ሕዝቡ ለንጉሡ፥ “በዳዊት ዘንድ ምን ክፍል አለን? በእሴይም ልጅ ዘንድ ርስት የለንም። እስራኤል ሆይ፥ ወደ ድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፤ ዳዊት ሆይ፥ አሁን የራስህን ቤት ተመልከት” ብለው መለሱለት። እስራኤልም ወደየቤታቸው ተመለሱ።
የእግዚአብሔርም ሰው በመሠዊያው ላይ፥ “መሠዊያ ሆይ፥ መሠዊያ ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ኢዮስያስ የሚባል ልጅ ለዳዊት ቤት ይወለዳል፤ ዕጣንም የሚያጥኑብህን የኮረብታ መስገጃዎቹን ካህናት ይሠዋብሃል፤ የሰዎቹንም አጥንት ያቃጥልብሃል” ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ጠራ።
ንጉሡ አሜስያስም ከኤፍሬም ከተሞች የመጡ ጭፍሮች ወደ ስፍራቸው ይመለሱ ዘንድ ለይቶ አሰናበታቸው፤ ስለዚህም ቍጣቸው በይሁዳ ላይ ጸና፤ ወደ ስፍራቸውም በጽኑ ቍጣ ተመለሱ።
ደግሞም ከኤፍሬም ልጆች አለቆች የአናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የመስለሞት ልጅ በራክያ፥ የሳሎም ልጅ ሕዝቅያስ፥ የአዳሊ ልጅ አማስያ ከሰልፍ የተመለሱትን ተቃወሙአቸው።
የኤፍሬምም ቅናት ይሻራል፤ የይሁዳም ጠላቶች ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።
የዳዊትንም ክብር እሰጠዋለሁ፤ ይገዛል፤ በአገዛዝም የሚበልጠው የለም። የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል፤ የሚዘጋም የለም፤ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
እርሱም አለ፥ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? እግዚአብሔርን ታደክማላችሁ፤
እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
እንዲህም አለኝ፥ “ይህ ሕዝብ፦ ከባድ ነው የሚለውን ሁሉ፦ ከባድ ነው አትበሉ፤ መፈራታቸውንም አትፍሩ፤ አትደንግጡም።
የዳዊት ቤት ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይነድድና ማንም ሳያጠፋው እንዳያቃጥል፥ በማለዳ ፍርድን አድርጉ፤ የተነጠቀውንም ከአስጨናቂው እጅ አድኑ።
ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤል ቤትና ይሁዳም በተንኰል ከበቡኝ፤ አሁንም እግዚአብሔር ዐወቃቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።