በስምንተኛውም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነርሱም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔርም ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ደስ ብሏቸው፥ ሐሴትም አድርገው ወደ እየቤታቸው ሄዱ።
ኢሳይያስ 63:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስጦታው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና ዐሰብሁ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ወገኖች እውነተኛ ፈራጅ ነው፤ እንደ ቸርነቱና እንደ ጽድቁ ብዛትም ይቅርታውን ያመጣልናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ እግዚአብሔር ስላደረገልን ሁሉ፣ ስለሚመሰገንበት ሥራው፣ እንደ ፍቅሩና እንደ ቸርነቱ መጠን፣ ለእስራኤል ቤት ያደረገውን፣ አዎን፣ ስላደረገው መልካም ነገር እናገራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ስላደረገልን ሁሉ፥ የጌታን ቸርነትና የጌታን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን የተትረፈረፈ ጽኑ ፍቅር እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኛ ስላደረጋቸው ድርጊቶች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሕዝብ እንደ መሐሪነቱ ስላሳየው ከፍተኛ በጎ አመለካከት፥ ስለ ተትረፈረፈውም ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የእግዚአብሔርን ቸርነት ምስጉን ድርጊቶቹን እዘረዝራለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፥ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ። |
በስምንተኛውም ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነርሱም ንጉሡን መረቁ፤ እግዚአብሔርም ለባሪያው ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ በልባቸው ደስ ብሏቸው፥ ሐሴትም አድርገው ወደ እየቤታቸው ሄዱ።
በሰባተኛውም ወር በሃያ ሦስተኛው ቀን ሕዝቡን ወደ ድንኳናቸው አሰናበተ፤ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለሰሎሞን፥ ለሕዝቡም ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት በልባቸው ደስ ብሎአቸው ሄዱ።
ምሽጎቹንም ከተሞች፥ መልካምን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጕድጓዶች፥ የወይኖቹንና የወይራዎቹን ቦታዎች፥ ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፤ በሉም፤ ጠገቡም፤ ወፈሩም፤ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።
ስለዚህ በሚያሠቃዩአቸው ሰዎች እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው፤ አስጨነቋቸውም፤ በመከራቸውም ጊዜ ወደ አንተ ጮኹ፤ ከሰማይም ሰማሃቸው፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት ታዳጊዎችን ሰጠሃቸው፤ ከሚያሠቃዩአቸውም እጅ አዳንሃቸው።
በመንግሥትህም በሰጠሃቸው ታላቅ በጎነትህ፥ በፊታቸውም በሰጠሃቸው በሰፊውና በሰባው ምድር አልተገዙልህም፤ ከክፉም ሥራቸው አልተመለሱም።
ዮቶርም እግዚአብሔር ያደረገላቸውን ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ እንደ አዳናቸው ሰምቶ በሁሉ አደነቀ።
ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፤ ባረክሁትም፤ ወደድሁትም፤ አበዛሁትም።
ተራሮችን እንዳልቀሥፋቸው እንዳላፈልሳቸውም፥ ኮረብቶችም እንዳይነዋወጡ እንደ ማልሁ እንዲሁ ከእኔ ዘንድ ያለሽ ይቅርታ አያልቅም፤ የሰላምሽ ቃል ኪዳንም አይጠፋም፤ መሓሪሽ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
ክፉ ሰው መንገዱን፥ በደለኛም ዐሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፤ እርሱም ይምረዋል፤ እርሱ ብዙ በደላችሁን ይተውላችኋልና።
በቸርነትህ የሚታገሡ መንገድህንም የሚያስቡ ይገናኙሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ፤ እኛም ኀጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ በሰማያት ያለው አባታችሁ ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መልካም ነገርን ይሰጣቸው!
ወይስ በቸርነቱ ብዛት በመታገሡ፥ ለአንተም እሺ በማለቱ እግዚአብሔርን አላዋቂ ልታደርገው ታስባለህን? የእግዚአብሔርስ ቸርነቱ አንተን ወደ ንስሓ እንዲመልስህ አታውቅምን?