ኢሳይያስ 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይተዋልና ጠፍቻለሁ፣ ወዮልኝ!” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን ስላዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርም የቆመበትን ቦታ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ፥ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።
ደግሞም፥ “እኔ የአባቶችህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን መለሰ።
ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፥ “ጌታ ሆይ፥ እማልድሃለሁ፤ ትናንት፥ ከትናንት ወዲያ ባሪያህን ከተናገርኸኝ ጀምሮ አፈ ትብ ሰው አይደለሁም። እኔ አፌ ኰልታፋ፥ ምላሴም ተብታባ የሆነ ሰው ነኝ።”
ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች አልሰሙኝም፤ እንዴትስ ፈርዖን ይሰማኛል? እኔም አንደበተ ርቱዕ አይደለሁም” ብሎ ተናገረ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከንፈሮቹ ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከንቱ ያመልኩኛል፤ ሰው ሠራሽ ትምህርትም ያስተምራሉ፤
እጃችሁ በደም ጣታችሁም በኀጢአት ተሞልትዋል፤ ከንፈራችሁም ዐመፅን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ኀጢአትን አሰምቶአል።
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹሞችዋን፥ ኀያላኖችዋንም አሰክራለሁ፤ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
“የሰው ልጅ ሆይ! በዐመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፤ እነርሱ ያዩ ዘንድ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፤ ይሰሙም ዘንድ ጆሮ አላቸው፤ ነገር ግን አይሰሙም፤ እነርሱ ዐመፀኛ ቤት ናቸውና።
ሕዝብ እንደሚመጣ ወደ አንተ ይመጣሉ፤ እንደ ሕዝቤም በፊትህ ይቀመጣሉ፤ ቃልህንም ይሰማሉ፤ ነገር ግን አያደርጉትም፤ በአፋቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባቸውም ጣዖታትን ይከተላልና።
እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴዎንም፥ “አቤቱ! አምላኬ ሆይ! ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ።