Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የመ​ድ​ረ​ኩም መሠ​ረት ከጩ​ኸ​ታ​ቸው ድምፅ የተ​ነሣ ተና​ወጠ፤ ቤቱ​ንም ጢስ ሞላ​በት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የመድረኩ መሠረት ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከድምፃቸው ጩኸት የተነሣ የቤተ መቅደሱ መድረክ እስከ ሥር መሠረቱ ተናወጠ፤ ቤተ መቅደሱም በጢስ ተሞላ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 6:4
12 Referencias Cruzadas  

ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኀይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፤ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።


በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።


የኪ​ሩ​ቤ​ልም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ረው ያለ ድምፅ እስከ ውጭው አደ​ባ​ባይ ድረስ በሩቅ ይሰማ ነበር።


መለ​ከ​ቱ​ንም የሚ​ነፉ መዘ​ም​ራኑ በአ​ን​ድ​ነት ሆነው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር ነውና፥ ምሕ​ረ​ቱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ” እያሉ በአ​ንድ ቃል ድም​ፃ​ቸ​ውን ወደ ላይ ከፍ አድ​ር​ገው በመ​ለ​ከ​ትና በጸ​ና​ጽል፥ በዜ​ማም ዕቃ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ባመ​ሰ​ገኑ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የክ​ብሩ ደመና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሞላው።


ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ሠ​ው​ያው ላይ ቆሞ አየ​ሁት፤ እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “አበ​ቦች የተ​ሳ​ሉ​ባ​ቸ​ውን ምሰ​ሶ​ዎ​ችን ምታ፤ መድ​ረ​ኮ​ቹም ይና​ወ​ጣሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ቍረጥ፤ እኔም ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ሩ​ትን በሰ​ይፍ እገ​ድ​ላ​ለሁ፤ ከሚ​ሸ​ሹ​ትም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ ከሚ​ያ​መ​ል​ጡ​ትም የሚ​ድን የለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥር​ዐት ቅን ነው፥ ልብ​ንም ደስ ያሰ​ኛል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይ​ኖ​ች​ንም ያበ​ራል።


ሲሄ​ዱም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራ​ዊ​ትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።


መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤


በሰ​ሜ​ኑም በር መን​ገድ በቤቱ ፊት አገ​ባኝ፤ እኔም አየሁ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መል​ቶት ነበር፤ እኔም በግ​ም​ባሬ ተደ​ፋሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios